ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር ለመቄት ነዋሪ እና ከተለያዬ ቦታ በጦርነቱ ተፈናቅለው ለመጡ 800 አባውራና እማውራዎች እገዛ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር ለመቄት ነዋሪ እና ከተለያዬ ቦታ በጦርነቱ ተፈናቅለው ለመጡ 800 አባውራና እማውራዎች እገዛ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የ ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር በጎጃም በመዞር በደቡብ ጎንደር በማድረግ ለሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት እና አግሪት ከተማ ከተለያዬ ቦታ በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው ለመጡ ወሀኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ይኸውም ከመቄት፣ ጋሸና፣ ገረገራ፣ ራያ፣ ዋድላ፣ አንጎት፣ ጋዞ፣ ቡግና፣ ላስታ፣ ላሊበላ እና ደሀና አካባቢ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉና ቤተሰቦቻቸው ለሞቱባቸው እንዲሁም ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው፤ ለእመጫት፣ ነፍሰጡር እና በእድሜ ለገፉ በአጠቃላይ ለ800 አባውራ 200 ኩንታል እስከ 800, 000 ብር /ስምንት መቶ ሺ ብር/ በላይ ወጭ በማድረግ ለአንድ የቤተሰብ አባላት 25 ኪሎ የስንዴ ዱቄት ማከፋፈሉን ገልጧል። በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በገንዘብ መደገፋቸውን የገለጸው ወሎ ቤተ አምሐራ ለለጋሾች ምስጋና አቅርቧል። ማህበሩ በደረሰበት ቦታ ሁሉ እንደታዘበው የጉዳት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ አሁንም እገዛችሁ አይለየን፤ መንግስትም የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ ችገር ላጋጠመው የአማራ ህዝብ እንዲደርስ እንጠይቃለን ብሏል። ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር ለመቄት ነዋሪ እና ከተለያዬ ቦታ በጦርነቱ ተፈናቅለው ለመጡ 800 አባውራና እማውራዎች እገዛ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የ ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር በጎጃም በመዞር በደቡብ ጎንደር በማድረግ ለሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት እና አግሪት ከተማ ከተለያዬ ቦታ በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው ለመጡ ወሀኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ይኸውም ከመቄት፣ ጋሸና፣ ገረገራ፣ ራያ፣ ዋድላ፣ አንጎት፣ ጋዞ፣ ቡግና፣ ላስታ፣ ላሊበላ እና ደሀና አካባቢ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉና ቤተሰቦቻቸው ለሞቱባቸው እንዲሁም ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው፤ ለእመጫት፣ ነፍሰጡር እና በእድሜ ለገፉ በአጠቃላይ ለ800 አባውራ 200 ኩንታል እስከ 800, 000 ብር /ስምንት መቶ ሺ ብር/ በላይ ወጭ በማድረግ ለአንድ የቤተሰብ አባላት 25 ኪሎ የስንዴ ዱቄት ማከፋፈሉን ገልጧል። በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በገንዘብ መደገፋቸውን የገለጸው ወሎ ቤተ አምሐራ ለለጋሾች ምስጋና አቅርቧል። ማህበሩ በደረሰበት ቦታ ሁሉ እንደታዘበው የጉዳት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ አሁንም እገዛችሁ አይለየን፤ መንግስትም የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ ችገር ላጋጠመው የአማራ ህዝብ እንዲደርስ እንጠይቃለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply