ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 1.1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የፍራሽ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 5 ቀን…

ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ማህበር በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 1.1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የፍራሽ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደብረብርሃን ከተማ መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ አንድነት ትምህርት ቤት፣ መምህራን ኮሌጅ፣ ዲያስፖራ ካምፕ፣ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደረገው ድጋፍም:_ 300 የእስፖንጅ ፍራሽ፣ 300 ብርድ ልብስ፣ 100 ኩንታል በላይ ለአዋቂ ሴቶች እና ወንዶች ለልጆች እና ህፃናት አልባሳት እና ጫማ እንዲሁም ሌሎች ምግብ ነክ ድጋፎችን አበርክቷል። በጎ አድራጎቱ ማህበሩ ድጋፉን ለተጎጅዎች ባደረሰበት ወቅትም የሰሜን ሸዋ የመንግስት አመራሮች ላደረጉላቸው ትብብር የመስግነዋል። የማህበሩ አባላት የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪ ለወሎ ተፈናቃዮች እስከ አሁን ድረስ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን መስክረዋል፤ ዳሩ ግን የሁሉም ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ ጥሪ አድርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply