ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በዋድላ ወረዳ በጦርነቱ ተፈናቅለው በዋሻ ሲኖሩ ከነበሩ አርሶ አደሮች መካከል ለ28 አባዎራዎች በበጎ ፈቃደኞች ትብብር መኖሪያ ቤት የተሰ…

ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በዋድላ ወረዳ በጦርነቱ ተፈናቅለው በዋሻ ሲኖሩ ከነበሩ አርሶ አደሮች መካከል ለ28 አባዎራዎች በበጎ ፈቃደኞች ትብብር መኖሪያ ቤት የተሰራላቸው መሆኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 3/2015 በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 017 ቀበሌ በመገኜት የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት እና በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን /ECNAS / አምና ሚያዝያ 10/2014 ዓ.ም የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ ያደረጉላቸው ወገኖች ከዋሻ ወጥተው ወደ ተሠራላቸው ቤት መግባታቸውን የወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አባላት የመስክ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን አስታውቋል። ዋድላ ወረዳ ባለፈው ዓመት 5 ግዜ ጦርነት የተደረገበት እና ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት በመሆኑ ከሌሎች አካባቢዎች በከፋ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ መኖሪያ ቤት በከፍተኛ ቁጥር የወደመበት መሆኑንም ጠቁሟል። አጠቃላይ በወረዳው 2,776 ቤት የወደመ ሲሆን እስከ አሁን በተለያዩ አካላት 200 ቤቶች ብቻ ናቸው የተሰሩት ያለው ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ከዚህ ውስጥ ለ28 አባወራወች 600,000 ብር /ስድስት መቶ ሺህ ብር / ወጭ በማድረግ ለ1 አባውራ 42 የቤት ቆርቆሮ በመለገስ 28 በዋሻ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን ህይወት መቀየር ተችሏል ሲል አክሏል። የወረዳው ኃላፊ አቶ ቧያለው “ድጋፍ ከማድረግ በዘለለ ድጋፍ የተደረገው ሀብት ምን ደረሰ ወገኖች ተጠቃሚ ሁነዋል ብላችሁ ለማየት መምጣታችሁ ከልብ እናመሠግናለን በቀጣይም ከፍተኛ ችግር ላይ ያሉ ወገኖች ስላሉ እገዛው ቀጣይ እንዲሆን ጥሪ አቀርባለሁ ” ብለዋል። ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት የደገፋችሁ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ከልብ እያመሰገነ ይሄ ድጋፍ እንዲሳካ ትብብር ያደረጉ በካናዳ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን / ECNAS/ ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖች ስም ያመሰገነው ድርጅቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000347415891 “ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት” ብሎ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply