ወሎ ዩንቨርስቲ በአይነቱ ለየት ያለ የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ኮንፈረንስ ፌስቲቫል ሊያዘጋጅ ነው፡፡ ዩንቨርሲቲው የሚያዘጋጀው የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ኮንፈረንስና ፌስቲቫል በአዲስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/X72P3-6StwTz8wo_NZ3UeNQGMwrQ2S8B3cnvZ3xyZZFyX5VvTtjSWDxLT_GdvlMdBtxrjt6yXXmYTmInTWO04fTOMeDKscJV7Jt7zbthKVI-Y_2D0UeYL0pPxPVRlfTTEjzHViFaHE2P82xEJQmC-jkuHLinFHUX6JTHtwsmaACCA5DIMOHwlEr2T9Ls7xKuJj8i8gexGl2S4aNfAUcRbcEaIcN5gUNsX6szbXfW2xkfW4kAo96JQHXR-79yn-q0jJQJPHcKg0Pe3ckFeU5vT7R8DJPCkE9j20vn5N1Cth8CFIYutPCD7EqD_xcM1c1ZMjxSv037T40-YBa5rIvHDg.jpg

ወሎ ዩንቨርስቲ በአይነቱ ለየት ያለ የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ኮንፈረንስ ፌስቲቫል ሊያዘጋጅ ነው፡፡

ዩንቨርሲቲው የሚያዘጋጀው የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ኮንፈረንስና ፌስቲቫል በአዲስ አበባና በደሴ ከተሞች እንደሚካሄድ ታውቋል።
በዝግጅቱ ላይ የባህል ፌስቲቫል፣ የጉዞ ፌስቲቫል፣ የፈረስ ግልቢያ ፌስቲቫልና የሙዚ ፌስቲቫል እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ከታህሳስ 19 እስከ 23 ድረስ በአዲስ አበባ እንዲሁም ከታህሳስ 29 እስከ ጥር 06 ድረስ ደግሞ በደሴ ከተማ ኮንፍረንና ፌስቲቫሉ ይካሄዳል ተብሏል።
ወሎ የመንግስትና የሃይማኖት ማዕከል ሆኖ መቆየቱን ያስታወሰው ዩንቨርስቲው ይሁን እንጅ የአካባቢው እምቅ ሀብት በሚፈለገው መልኩ አልተዋወቀም ብሏል።

በመሆኑም ይህ ኮንፍረንስና ፌስቲቫል አካባቢውን ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ነው ያለው።
በደሴና በአዲስ አበባ ከተሞች የሚካሄደውን ፌስቲቫል ወሎ ዩንቨርስቲ ከቫይብራኒየም ሪሶርስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እንደተዘጋጀም ታውቋል።

ታህሳስ 29/2015 ዓ.ም በደሴ ከተማ በሚጀመረው ፌስቲቫል ላይ አንጋፋዋ አርቲስት የክብርት ዶክተር ማሪቱ ለገሰ የሙዚቃ ስራዎቿን እንደምታቀርብም ወሎ ዩንቨርስቲው በመግለጫው አንስቷል፡፡

በአባቱ መረቀ
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply