ወራሪው ትህነግ ግድያ እና ተራ ዝርፊያ እየፈፀመ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወራሪው…

ወራሪው ትህነግ ግድያ እና ተራ ዝርፊያ እየፈፀመ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወራሪው ትህነግ ግድያ እና ተራ ዝርፊያ እየፈፀመ መሆኑን የገለፀው የአማራ ክልል መንግስት ክልሉ የህልውና ዘመቻውን ህዝባዊ ማድረጉን ተከትሎ ዝርፊያና ግድያው ጠላት በሁሉም ግንባሮች እየደረሠበት ባለው ሽንፈት ተስፋ መቁረጡን ማሳያ ነው ብሏል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በመልዕክታቸው በህልውና ዘመቻው ሁሉም የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል። ወጣቶች ግንባር በመዝመት፣ ማህበረሠቡ በስንቅ ዝግጅትና ደጀንነት የሚጠበቅበትን እየተወጣ ነው ሲሉ አክለዋል። ዲያስፖራው ገንዘብ በማሠባሠብና የዓለም ማህበረሠብን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር እንዲሠሩ የተሠጣቸውን ተልዕኮም እየተወጡ ነው ብለዋል። በየግንባሮቹ በጠላት ላይ እየደረሠ ባለው ሠብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ላይ ስለመሆኑ እያደረሠ ያለው ዝርፊያና ጅምላ ግድያዎች ማሳያ ነው ብለውታል። ጠላት ሠርጎገቦችን ወደ ክልሉ በማስገባት እና የፕሮፖጋንዳ ስራዎች ከጦርነቱ ባልተናነሠ እየሠራ ቢሆንም እስከመጨረሻው የድል እወጃ ድረስ ሁሉም የድርሻውን እየተወጣ በመሆኑ ሊሳካ አልቻለም ያሉት አቶ ግዛቸው በዘመቻው ህዝባዊነት ላይ ወጣቶች ሠርጎገቦችን ለህግ የማቅረቡ ሂደት መረጃ የማጣራት ብስለትና ትዕግስት እንዲታከልበት አሳስበዋል። መረጃውን ከማጠናቀር አማራ ኮሚዩኒኬሽንን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply