“ወራሪ እና ከሃዲ ጁንታን በመጣበት እንቀብረዋለን” የኪንፋዝ በገላ ነዋሪዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማዕከላዊ ጎንደር…

“ወራሪ እና ከሃዲ ጁንታን በመጣበት እንቀብረዋለን” የኪንፋዝ በገላ ነዋሪዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ ግንባር እየተመሙ እንደሚገኙ ተነግሯል። ጀግናው የኪንፋዝ በገላ ህዝብ “እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም፤ ወራሪ እና ከሃዲ ጁንታን በመጣበት እንቀብረዋለን” በሚል ወኔ ወደ ግንባር እየዘመተ ነው። የውሰጥ እና የውጭ ባንዳን ዛሬም እንደትናንቱ እናሸንፋለን፤ በድል እንወጣለን የሚሉት የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ጀግኖች ጉዟቸው ወደ ግንባር ሆኗል። አሸባሪው ትሕነግ በተለያዩ የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች የከፈተው ጦርነት ከፍ ያለ ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ ግልጽ ነው። የሽብር ቡድኑ በተቆጣጠራቸው የራያ ቆቦ አካባቢዎች ግን በንጸሃን ላይ እንደለመደው ከፍተኛ ግፍ መስራቱን ቀጥሎበታል እየተባለ በመሆኑ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply