ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች በተፍጥሯቸው የሀገራትን ወሰን አያውቁም፡፡

ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች በተፍጥሯቸው የሀገራትን ወሰን አያውቁም፡፡ ነገር ግን ባያውቁም ለአገራት እና ህዝቦች ካላቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ እና ባህላዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ጥቅም አኳያ በአገራት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ውጭ ጉዳይ ፖሊስ ዋና አካል ይሆናሉ፡፡

በዚህም ምክንያት የሰለጠነው ዓለም በእንደዚህ አይነት ወሰን ተሸጋሪ ወንዞች ባህሪ ላይ ጫፍ እና ጫፍ የቆመ አቋም አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ለግጭት እና ለጦርነት መሰረቶች፣ መሳሪያዎች እና ምክንያቶች ናቸው ሲሉ የሚከራከሩ ምሁራን እንዳሉ ሁሉ) ሌሎቹ ደግሞ ወሰን ተሸጋሪ ወንዞች በአገራት መካከል ግጭት መቀነሻ እና የትብብር እና አንድነት ማቀጣጠያ መሰረቶች ናቸው ይላሉ፡፡

ዋናው ነገር ወሰን ተሸጋሪ ወንዞች የግጭት ምንጭ/ምክንያት እንዲሁም የትብብር መሰረት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዋናው እና ትልቁ ነገር በአገራት መካከል ያለ ታሪካዊ ግንኙነት፣ የአቅም ሚዛን፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ማህበራዊ እና ባህላዊ/ሃይማኖታዊ መስተጋብሮች  እንዲሁም የአገዛዝ ዓይነቶች እና የመንግስታት ባህሪ ዋና ዋና ጉዳዮች እና ተጽእኖ አሳዳሪ ነገሮች ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ወሰን ተሸጋሪ ወንዞችን ስንመረምር ኤፍራጠስ-ጢግሮስ፣ ዮርዳኖስ እንዲሁም አባይ/ናይል ከትብብር ይልቅ ለግጭት ቅርቦች ናቸው፡፡

እንደ አባይ-ናይል ተፋሰስ እጅግ በጣም መራራ ጦርነቶችን ያስተናገደ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ጦርነቶች ይካሂያዳሉ፡፡ ባህርያቸውም አይቀየርም ምክንያታቸው እና አድራጊያቸው ይለያይ እንጅ፡፡ የአባይ ተፋሰስ የጦርነት ማስተናገድ ልዩ የሚሆነው ምክንያት ግን እራሱ አባይ የጦርነቱ ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ ሌሎች አገራትም በዚህ ጉዳይ ላይ አይን እና ቀልባቸው ይሳባል ጣልቃ ለመግባት ኢትዮጵያን ለመጫን ይሞክራሉ አይሳካላቸውም አንጂ የዛሬው ኢትዮጵያዊ ወንዞች ዝግጅታችንም ከቀደምት ጊዜያት  ጀምሮ ያለውን የርእዮተ አለም አሰላለፍ ሂደት ይቃኛል፡፡

ቀን 06/05/2013

አዘጋጅ፡ሊዲያ አበበ!!

ኢትዮጵያዊ ወንዞች

Source: Link to the Post

Leave a Reply