You are currently viewing ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከቤተ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ)ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ ጦርነት እንደ ሀገር ፈታኝ ወቅት…

ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከቤተ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ)ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ ጦርነት እንደ ሀገር ፈታኝ ወቅት…

ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከቤተ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ)ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ ጦርነት እንደ ሀገር ፈታኝ ወቅት ላይ አናገኛለን። ይህንን የሀገራችንና የህዝባችን ፈታኝ የሆነበትን አስከፊ ዘመን እንደ አባቶቻችን በጥበብ መሻገር ካልቻልን የታሪክ ስህተት እንዳንሰራ እንፈራለን ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የአውሮፓና የምራባውያንን ተልእኮ በመሸከም ሀገር እንድትፈርስ ፣ ህዝብ እንድበተን እየሰሩ ያሉ ባንዶች መኖራቸው ይታወቃል ።የትግራይ ወራሪ ቡድን የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከከፈተስት ወቅት ጀምሮ የውስጥ ባንዶች በመሰባሰብ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል መባት ካለብን ሲኦል ድረስ አንገባለን በማለት አቅማቸውን አሟጠው የነጮችን ሀገር አፍራሽ ሴራ አንግበው እናት ሀገር ኢትዮጵያን ለዘርፈ ብ…ዙ ችግሮች ዳርገዋታል። አሁንም ቢሆን በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ባሉ አንዳንድ ሀገር ጠል በሆኑ ግለሰቦች የሚደገፈው በምክር ቤት ደረጃ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የኦነግ ሼኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በተለይም በወለጋ አካባቢ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በእጅጉ ያሳስበናል። የትግራይ አሸባሪ ቡድን በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው ሰብአዊ ማህበራዊና ፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በእጅጉ መንግስት ሊያላስበው ይገባ ነበር።ነገር ግን እየሆነ ያለው ከዚህ በተቃራኒ መሆኑ እንደ ህዝብ የአማራ ህዝብ ሀገር ለመታደግ እየከፈለ ያለውን መስዋእትነት በመንስት በኩል ዋጋ አለመስጠት አንዳለ በግልፅ እየታየ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህ አሸባሪ ቡድን በህዝባችን ላይ ኢሰብአዊ ድር ቶች ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል። የሚገርመው አሁንም የሰቆቃው ቆይታ በወሎ የራያ አማራዎች ላይ እንደቀጠለ መሆኑ የበለጠ ችግሩን አንገብጋቢና አስከፊ አድርጎት ይገኛል ። በመሆኑም የአማራ ህዝብ በዚህ ወቅት ከመቸውም ጊዜ በላይ እየተፈተነ የሚገኝበት ወቅት ነው ፡፡ በየትኛውም የሀገሪቱ ከፍል የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ውሰጥ ነው ያለው።ለአማራ ህዝብ መሸለም ቢቀርበት ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንደሚባለው ሀብት ንብረቱ እየተዘረፈ፣ እየተገደለ ፣ ከእርስቱ እየተፈናቀለ ያለበት ሁኔታ መፈጠሩ ያሳዝናል። አማራ መገደሉ ሀብቱ መዘረፉ ሳያንስ ሬሳውንም በቅጡ አፈር እንድለብስ አይፈቅዱለትም። በአራቱም ቅጣጫ በሽዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በየቀኑ እንደበግ እየታረዱ ይገኛሉ ፡፡ በሚሊዮን የሚሆኑ አማሮች ቀያቸውን ለቀው ጎዳና ላይ ወድቀው ይገኛሉ።ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት የአማራ ህዝብ አንድ አድረጎ ማንነቱን እንዲያስክብር ማድረግ ሲገባ ለመጣው ሁሉ ሞግዚት መሆን የማይሰለችው ብአዴን አንቂና ታጋይ የአማራ ልጆችን እያሳዳደ እያሰረና እየገደለ መሆኑ ጕዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል። ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ ሌሎች የአማራ ልጆችን የአማራን ባህልና ክብር በማይጠብቅ መልኩ በአባቶችን ወግ መሰረት ሽምግልና በሚል ሽፋን ከጠራ በኋላ ማሰሩ እጅግ አሳፋሪ ነው።መንግሥትም የአማራን ህዝብ መናቁና ወግና ስርአቱንም ማዋረድ መሆኑን አመላካች ነው ። የወሎ አማራ ( ራያ ) አሁንም በጠላት ወረራ ህዝባችን እየተገደለ ንብረቱ እየተቃጠለና እየተዘረፈ ባለበት ወቅት መንግስት የአማራ ልጆችን ማሳደዱ መንግስትም ቢሆን የአማራን ህዝብ ሰቆቃ አንድቀጥል እየሰራ ያለበት ሁኔታ ያለ ይመስላል ። ይህንን መሰረት በማደረግና ህዝባችንን ከዳግም ወረራ ለመታደግ የሚከተሉትን ባለ 5 ነጦቦች ያሉት የአቋም መለጫ ውጥተናል ። 1.መግንስት እውነት የህዝብ ተወካይ እና አገልጋይ ከሆነ ወራሪውን የትግራይ ሃይል የሚከፈለውን ዋጋ ከፈሎ ከራያ እንዲያስወጣና ዳግም ለአማራና ለኢትዮጵያ ህዝብ ስጋት የማይሆነበት ደረጃ እንዲደርስ ማደረግና ለህዝባችን ሰላም ማሰፈን አለበት። 2.የአርበኛ ዘነመ ካሴን ጕዳይ የተቋረጠው ድርድር እንዲታይና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እንጠይቃለን ፡፡ 3. በኦሮሚያ ከልል በማነታቸው ምክንያት በኦነግ ሰራዊት ስለሚገደለውና ስለሚፈናቀለው የአማራ ህዝብ የፌደራል መንግሰት የማያዳግም አስቸኳይ መፍትሔ እድወስድ አንጠይቃሰን፡ 4.በአድስ አበባ ከተማ ጋዜጠኞች እና ማህበረሰብ አንቂዎችን ከመንግስት በላይ ህወሃትን አምርረው መታገላቸው እየታወቀ የህወሃት ተላላኪናችሁ ብሎ ማሰር የለየለት ፀረ – ህዝብ መሆኑ ታውቆ በእስቸኳይ ፍትህ እንዲገኙ አንጠይቃሰን፡ 5.በአማራ ከልል ፋኖ ናችሁ በማለትና የነቁ አማሮችን በየአካባቢው እያሳደዱ ማፈን ህዝባችን ላይ ሌላ ችግር ለፍጠር የሚሰሩ በየደረጃው ያሉ የከልል የመንግስት አመራሮች እየሄዱበት ያለው መንገድ አግባብነት ስሰለው ከድርጊታቸው እንድቆጠቡና መንግስት አካሄዱን አድያስተካከል እንጠይቃለን ፡፡ ከላይ የተቀመጡትን የአቋም መግለጫ ነጦቦች መንግሰት በአስቸኳይ ፍትሔ የማይሰጥባቸው ከሆነ ህዝባችንን ከሞትና ከስደት ለመታደግ ሌሎች አማራችን የምነጠቀም መሆኑን እንገልፃለን፡ አንድ አማራ ‼️ ቤተ አምኃራ ( ወሎ ) ደሴ መስከረም 14 / 2015 ዓ.ም አርበኝነት የማንነታችን አርማ ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply