ወታደራዊ ትግል እና ሚስጢር ======= ሸንቁጥ አየለ ========= 1፡መሪህን ደብቅ።ጠላት መሪህን ለማወቅ በሚያደርገዉ ጥረት ዉስጥ መሪህን መለዬት እንዳይችል ብዙ አደናጋሪ መሪዎችን ሆን…

ወታደራዊ ትግል እና ሚስጢር ======= ሸንቁጥ አየለ ========= 1፡መሪህን ደብቅ።ጠላት መሪህን ለማወቅ በሚያደርገዉ ጥረት ዉስጥ መሪህን መለዬት እንዳይችል ብዙ አደናጋሪ መሪዎችን ሆን ብለህ ሰይም 2፡ወታደራዊ ድርጅትህን በጥብቅ መርህ ላይ አቁመዉ 3፡የምታወጣቸዉን መርሆችም በፍጹምነት እስፈጽማቸዉ 4፡የገንዘብ ወይም የቁስ ወይም የሀሳብ ወይም የመረጃ ስጦታዎችን ዝም ብለህ ከማታዉቀዉ ምንጭ ሁሉ አትቀበል።ማንኛዉንም ስጦታ አንተ በምትቆጣጠረዉ ሁኔታ ብቻ ተቀበል 5፡ልትቆጣጠራቸዉ ከምትችላቸዉን ሚዲያዎች ጋር ብቻ ስራ። 6፡የህዝብ ድጋፍ በህዝብ ይሁንታ ቢገኝም ይሁንታዉን የምታገኝበታ eዉነታ ግን ቁልፉ የድጋፉ መሰረት ነዉ 7፡ወታደራዊ ትግልህ ለብዙሃኑ ህዝብ ተስፋ የሰነቀ ይሆን ዘንድ ከፍ ባለ አላማ ላይ አቁመዉ 8፡በምንም መልኩ በትግሉ ከሚተዳደሩ ፡ በትግሉ ከሚነግዱ እና እራሳቸዉን ችለዉ ከማይችሉ ግለሰቦችና ሚዲያዎች የትግልህን እዉነተኛ መረጃ አርቅ።የግድ እነዚህን የምትጠቀምበት ሁኔታ ዉስጥ ከሆንክም የምታቀርብላቸዉ መረጃ የተቆጠበና የትግል ሂደቱን ተቆጣጥረዉ ለጠላት ሊሸጡት በማያስችል መልክ ይሁን 9፡በተመሳሳይ የትግል መስመር ከተሰለፉ ወታደራዊ ድርጅቶች ጋር ቀድመህ ተግባባ። ህዝብን የሚመራና የሚያስተባብር አንድ ወታደራዊ ድርጅት ቢኖር ለብዙ ነገር መልካም ነዉ።ይሄም መሆን ካልቻለ ግን በተመሳሳይ አላማ ላይ ከቆሞ ሀይሎች ጋር በትብብር የምትሰራበትን ስልት የግድ መፍጠር እጅግ ወሳኝ ነዉ። 10፡ የትግሉ የገቢ ምንጭ ፍጹም በሆነ መልክ መድርጅቱ መታወቅ አለበት።ጠላትህን መዝረፍ፡ የንግድ ተቋማትን መመስረት፡ በምትቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች ፍጹም ዲሞክራሲያዊ ስር ኣeት በመዘርጋት ከህዝብ ተገቢ ታክስ መሰብሰብ፡ ከጠላት ጋር የተሰለፉትን ሀይሎች ወደ ዋና ከተማዎች በመግባት የትግሉ የገቢ ምንጭ ማድረግ፡ ከዉጭ ሀገር ደጋፊዎች ድጋፍ ማግኘት ወይም የትኛዉም የገቢ ምንጭ ቢሆንም የገቢህ ምንጭን በትክክል ማወቅ ካልቻልክ ወታደራዊ ምስጢርህን ስለመጠበቅህ እርግጠኛ ማሆን አትችልም። 11፡ የደርጅቱ መሪዎች ስልካቸዉ በዬሚዳዉ የተበተነ ከሆነ እና ማንም ደዉሎ ካገኛቸዉ ወታደራዊ ሚስጢር የባቄላ ወፍጮ ሆኗል ማለት ነዉ።ይሄን አስተካክል 12፡ እርግጠኛ የታመኑ ደጋፊዎችህ የግድ መሪዎችህን ማግኘት አለብን ካሉ አሁንም ይሄ ሂደት መከናወን ያለበት ድርጅቱ በሚቆጣጠረዉ ሁኔታ ብቻ መሆን አለበት 13፡ ነገ ሀገር እንደሚረከብ ሀይል እንጂ እንደ ሰፈር ቡድን የሚያስብ ሀይል ላለመሆን ጥንቃቄ አድርግ።በመሆኑም የሀገር ጥቅም የሚጎዱ ጉዳዮች ላይ ከቀኝም ከግራም አቋም እንድትወስድ ጉትጎታ ቢደርስብህም ነገሩን እያጠናንዉ ነዉ ብለህ አቋም ከመዉሰድህ በፊት ጊዜ በመዉሰድ የማንሰላሰል ድርጅታዊ ስራ ይሰራ 14፡ከሁሉም ከባድ የሚሆነዉ ይሄ ሁሉ የሚከወነዉ አንድ ወታደራዊ ድርጅት እጅግ ጭቅ በሆነ ሁኔታ ዉስጥ በሚመላለስበት ሁኔታ መሆኑ ነዉ::የፈለገ ያህል ጭንቅ ዉስጥ ቢሆንም ቅሉ ግን የአንድ ወታደራዊ ድርጅት ዉጤታማነት የሚለካዉ ብሎም እና ግብ ለመድረስ ቁልፍ ሚስጢሩ ሚስጢርን መጠበቅ፡ መስራት እና መቆጣጠር መቻሉ ይሆናል

Source: Link to the Post

Leave a Reply