ወንጀሎችን በምስል እና ድምጽ መጠቆም የሚያስችል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

ዓርብ ግንቦት 16 ቀን 2016 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) አበልፅጎ በማስመረቅ ሥራ አስጀመረ።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ መተገበሪያው ህዝብን ያሳተፈ ወንጀልን ለመቀነስ እና ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

እንዲሁም ዜጎች በቀላሉ የስርቆት ወንጀል፣ እገታ፣ አደጋ፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዲሁም ሌሎች የህግ አካላት የሚያስፈልጉበት ሁኔታዎችን ሲመለከቱ በጽሑፍ መልዕክት፣ በምስል እና በተንቀሳቃሽ ምስሎችን በቀጥታ ወደ ፌደራል ፖሊስ መላክ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ይኼውም ፌደራል ፖሊስ የተላከለትን መረጃ በመመልከት ለስፍራው ቅርብ የሆኑ የሕግ አካላትን በመላክ የሚፈጠሩ አደጋዎችን መቀነስ ያስችላል ተብሏል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የሕግ አካላት በዜጎች ላይ እየፈጸሙት ነው የሚባሉ ወንጀሎች መኖራቸውን በማንሳት “ማንኛውም ፖሊስ ዜጎችን እንዲያጎሳቁል ሕግን ባለተከተለ መንገድ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አይፈቀድለትም” በማለት “ለራስ ጥቅም ህዝብን መጉዳት ከወታደር አይጠበቅም” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተመርቆ ወደ ስራ የገባው መተግበሪያ ከመተግብሪያ ማወጃዎች አፕ ስሮር (App store) እና ከፕሌይ ስቶር (play store) አውርዶ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ወንጀልን ለመከላከል በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በሰነድ ወይም በነፃ 911 የስልክ መስመር በመደወል መሳተፍ እንደሚቻል ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply