You are currently viewing ወያኔ አማራን ለማጥፋት በተነሳበት ወቅት ከክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአሕድ) መስራችና አንጋፋ የመኢአድ አባልና አመራር በ…

ወያኔ አማራን ለማጥፋት በተነሳበት ወቅት ከክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአሕድ) መስራችና አንጋፋ የመኢአድ አባልና አመራር በ…

ወያኔ አማራን ለማጥፋት በተነሳበት ወቅት ከክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአሕድ) መስራችና አንጋፋ የመኢአድ አባልና አመራር በመሆን ሲታገሉ የኖሩት አቶ ተስፋዬ ደርቤ አርፈዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሎም የመላው ኢትዮጵያዊያን እኩልነት፣ አብሮነት፣ ወንድማማችነትና ነጻነት ይረጋገጥ ዘንድ አምባገነኑን የትሕነግ ቡድን ከስልጣነ መንበሩ ገለል ለማድረግ በተደረገው ትግል የራሳቸውን ጉልህ አስተዋጽኦ ካበረከቱት የተፈተኑና ፈተናውንም በብቃት ካለፉት መካከል አንዱ የሆኑት ታጋይ ተስፋየ ደርቤ አርፈዋል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ያዘጋጀው የአቶ ተስፋዬ ደርቤ አጭር የህይወት ታሪክ እንደሚከተለው ይቀርባል:_ አቶ ተስፋየ ደርቤ ከአባታቸው ከአቶ ደርቤ በርሶማ ከእናታቸው ከወ/ሮ ጌጤ ተክሌ በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር በመንዝ እና ግሼ አውራጃ በቀያ ገብርል በዘመሮ ወረዳ እንዶድ ጊዮርጊስ ደብር ከተባለው ቦታ ጥር 26 ቀን1944 ዓ.ም በዘመነ ዮሃንስ ተወለዱ። አስተዳደጋቸውም በመንፈሳዊ ትምህርት እና ከግብርና ስራ ጋር የተገናኘ ሲሆን እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ አካባቢያቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በደብረብርሃን ከተማ ሀይለማርያም ማሞ አጠቀላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተከታተሉ እያለ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ውጊያ ለውትድርና ተመልምለው ጥር 29 ቀን 1969 ዓ/ም በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በደብረብርሃን ከተማ ነበልባል ክፍለ ጦር ተቀጠሩ። በማሰልጠኛ ይሰጥ የነበረውን ወታደራዊ ትምህርት በበቂ ሁኔታ ከወሰዱ በኋላ ወደ ሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው በኤርትራ ክፍለ ሀገር በተለያየ አውደ ውጊያዎች ለምሳሌ በአካለ ጉዛይ ፣በከረን ፣በምጽዋ ፣ በአሰብ እና በሌሎችም ተሳትፈው የዜግነት ግዴታቸውን ተወጥቷል። አቶ ተስፋየ ደርቤ በዚያድባሬ ይመራ የነበረው የሶማሊያ መንግሥት ወራሪ ሀይል በምስራቅ ኢትዮጵያ የሀገራችን ዳርድንበር ጥሶ በገባበት ወቅት አቶ ተስፋየ በግንባር በመሰለፍ በድጋሚ ከወራሪው ጋር አንገት ለአንገት በመተናነቅ የጠላትን ጦር በመደምሰስ የሀገር ሉዓላዊነትን በደማቸው ካስከበሩ ጀግኖች አንዱ ነበሩ። አቶ ተስፋየ ደርቤ ትህነግ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ አማራን ለማጥፋት በተነሳበት ወቅት ከእውቁ የህክምና ባለሙያ ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት(መአሕድ) በ1984 ዓ/ም በመመስረት የአማራን እልቂት ለማስቆም ግንባር ቀደም ታጋይ ሆነው ትልቅ ዋጋ ከከፈሉት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዱ ነበሩ። በዚህ ጠንካራ አቋማቸው ለሰው ልጅ በነበራቸው ክብር ወያኔ ባለስልጣናትን ለመግደል እቅድ አዘጋጅተሃል በሚል በሀሰት 5 ዓመት ሙሉ በከርቼሌ አስሮ አሰቃይቷቸዋል። አቶ ተስፋየ ደርቤ ወያኔ በህዝብ እና በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል አእምሮአቸው ሊቀበለው ስላልቻለ ከመአሕድ ወደ መኢአድ የተደረገውን ሽግግር በሙሉ ልብ በመቀበል በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይደርስ የነበረውን ግፍ በመቃወም በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈውም ነበር። እንደገና ምርጫ 1997ን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ወያኔ ተስፋየ ደርቤንና መሰሎቹን ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ተንቀሳቅሰሃል በሚል የሀሰት ክስ አቅርቦ ከእነ ኢንጂነር ሀይሉ ሻውል ጋር በድጋሚ አስሯቸው ነበር። አቶ ተስፋየ ደርቤ ግፍን ፣በደልን አእምሯቸው የሚፀየፍ በመሆኑ ለ3ኛ ጊዜ በ2005 ዓ/ም ከሌሎች 9 የመኢአድ አመራሮች ጋራ አስሮ አሰቃይቷቸዋል። ህይወታቸውን ለትግል የሰጡት ተስፋየ ደርቤ ይህ ሁሉ እስር ፣ እንግልት ፣ ግፍ ሳይበግራቸው ከመላው አማራ ህዝብ ድርጅት እስከ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በጽናት ፣በታማኝነት እና በተነሳሽነት የደረሰባቸውን ሁሉ በመቻል ለሀገር እና ለህዝብ ባደረጉት ትግል የማይደበዝዝ ታሪካዊ ትግል አስመዝግበው አልፈዋል። ወያኔ በተለያዩ እስር ቤቶች ባደረሰባቸው ከባድ ጉዳት ምክንያት በህመም ቤታቸው እስከዋሉበትና ህልፈተ ህይወታቸው እስከተሰማበት ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) በአመራርነት እያገለገሉ ቆይተዋል። በመሆኑም መላው የድርጅታችን አባሎች፣ ደጋፊዎች የተሰማን ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለፅን ለሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እየተመኘን ፈጣሪ የእኒህን እውነተኛ የሰው ልጅ መብት ተሟጋች የሀገር አስከባሪ ነፍስ እረፍት ይሰጥልን ዘንድ እንማፀናለን። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ

Source: Link to the Post

Leave a Reply