ወደ ሱዳን የሸሹ ልዩ የፖሊስ አባላትና በጡረታ የወጡ የቀድሞ መከላከያ ጀነራሎች ሱዳን ድንበር አካባቢ እየተሰባሰቡ እንደሚገኙ ተገለጸ።…

ወደ ሱዳን የሸሹ ልዩ የፖሊስ አባላትና በጡረታ የወጡ የቀድሞ መከላከያ ጀነራሎች ሱዳን ድንበር አካባቢ እየተሰባሰቡ እንደሚገኙ ተገለጸ።…

ወደ ሱዳን የሸሹ ልዩ የፖሊስ አባላትና በጡረታ የወጡ የቀድሞ መከላከያ ጀነራሎች ሱዳን ድንበር አካባቢ እየተሰባሰቡ እንደሚገኙ ተገለጸ። አሻራ ሚዲያ 06/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር ወደ ሱዳን የሸሹ ልዩ የፖሊስ አባላትና በጡረታ የወጡ የቀድሞ መከላከያ ጀነራሎች ሱዳን ድንበር አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰባሰቡ መሆኑን ምንጫችን ገልጸዋል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ካርቱም ድረስ እጁን ማስገባት ሳይኖርበት አይቀርም ካልሆነ ዳግም ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉም ተናግረዋል። የግብጽ ደህንነት መስሪያ ቤት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ውር ውር ሲሉ መክረማቸውና በድንበር ላይ ባለች ገጠራማ ከተማ ውስጥ መደራጀት መጀመራቸውም ታውቋል። እንደምንጫችን ገለጻ እነዚህ አጥፊ ቡድን የሱዳንን ወታደር ልብስ ለብሰው ድንበር ሊሻገሩ ስለሚችሉ በሜካናይዝድ የታገዘ ጦር ድንበር አካባቢ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል። የሱዳን ወታደሮች በብር የሚገዙ ናቸው ያሉት ምንጫችን የከፋ ችግር ከመድረሱና ነገሩ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንዳይሆን መንግስት ልዩ ጥናቃቄ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply