ወደ ሶማሊላንዷ ሃርጌሳ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በሶማሊያ መንግሥት እንዲመለስ ተደረገበቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ወደተፈራረመችው ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ ሲበር የ…

ወደ ሶማሊላንዷ ሃርጌሳ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በሶማሊያ መንግሥት እንዲመለስ ተደረገ

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ወደተፈራረመችው ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የሶማሊያ አየር ክልል ውስጥ ከመግባቱ በፊት እንዲመለስ መደረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሃርጌሳ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ከሶማሊያ በኩል ፍቃድ የለውም በመባሉ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል።

የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 ፍቃድ ስላልነበረው ሃርጌሳ ላይ እንዳያርፍ መከልከሉን አስታውቋል።

መደበኛው የበረራ ቁጥር ኢቲ372 ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ሃርጌሳ ማረፉን የበረራ መከታተየ በሆነው ፍላይትራዳር አሳይቷል።

ይሁን እንጂ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 የሆነው ዲ ሃቪላንድ-400 አውሮፕላን ጠዋት 2፡30 ከአዲስ አበባ ተስቶ ወደ ሃርጌሳ አቅጣጫ እየበረረ ሳለ የጂግጂጋ ሰማይ ላይ በመዞር ረፋድ 4፡30 አካባቢ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ አርፏል።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ዘግይቶ በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 ፍቃድ ስላልነበረው ሃርጌሳ ላይ እንዳያርፍ መከልከሉን አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ እንዳለው የኢቲ 8273 በረራ ከሶማሊያ ማግኘት የነበረበትን ፈቃድ ስላልነበረው የዓለም አቀፍ የበረራ ሕግን በመተላለፉ ወደ አገሪቱ የአየር ክልል እንዳይገባ መደረጉን ገልጿል።

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply