መንግስት በዚህ ዓመት ከ600ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉ አስታውቋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ፣ በቀጣይ ሳምንት የመቁረጫ ነጥብ በማውጣት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከግዜ ቀደ ግዜ ወደ ቴክኒክና ሙያ የሚገቡ ዜጎች ቁጥጥር እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት ሚኒስትር ድኤታው በየዓመቱ በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡
ባለፉት 2 ዓመታት ወደ ተቋሙ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚገቡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከመደበኛ ተማሪዎች በተጨማሪ በአጫጭር ኮርሶች ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነዚህ ተቋማት በመግባት ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል፡፡
በሀገሪቱ ከ1800 በላይ የመንግስትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን፣ በነዚህ ተቋማት ውስጥ 30 ሺህ የሚደርሱ መምህራን አገልግሎት እንደሚሰጡ አንስተዋል፡፡
ነገር ግን ለዚህ ተቋም የሚሰጠው አመለካከት ተገቢ ያልነበረ ቢሆንም፣ አሁን አሁን የመቀየር አዝማሚያ እንዳለው ይናገራሉ፡፡
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው እንደ ቻይና ካሉ ሀገራት ጋር የልምመድ ልውውጥ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በተለይም በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ከ12 በላይ የሆኑ በቻይና ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post