ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገቡ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡

በሆስፒታሉ አስተኝቶ ህክምና ምክትል ዳይሬክተር ነርስ ተስፋዬ አለምነህ ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ አዳዲስ ታካሚዎች እየጨመሩ መምጣጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

በአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚመጡ ታካሚዎች ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉም ተብሏል።

ከሆስፒታሉ ደህና ሆነው ወተው ከወጡም በኋላ ያለው ሁኔታ የተስተካከለ ስለማይሆንላቸው ተመልሶ የማገርሸት እና ተመልሶ የመምጣት ነገር እየጨመረ መጥቷል ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አንድ ክፍተት እየፈጠረ ያለው የተጠኑ ጥናቶች ባለመኖራቸው መንግስትም ትኩረት እየሰጠው አለመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚመጡ አብዛኞቹ ታካሚዎች ድባቴ ፣ባይፖላር ፣ ከባድ የአእምሮ ህመምና በአደንዛዥ እፅ ሱስ ሳቢያ የሚመጣ የአዕምሮ ህመም የተጠቁ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከሚታከሙ ታካሚዎቸ ውስጥ በብዛት ከ20-40 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቁጥራቸው ከፍ እንደሚል አንስተዋል ፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታም በጣም የቆየ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ ተስፋዬ በተደጋጋሚ የአልጋ እጥረቶች እንደሚገጥሟች አስታውቀዋል፡፡

ለሚፈጠሩ ክፍተቶች እንደማስተንፈሻም በጤና ሚኒስተር አማካኝነት በሆስፒታሉ ግቢ ሌላ ህንፃ ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ መጣሉን እና በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ያልቃል ተብሎ እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

የአእምሮ ህመም ታክሞ መዳን የሚችል በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባም ተግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply