ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ፍተሻዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ወደ ከተማ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/g1pRMeMkzcpckZB4t8AKfo-swNdtaiVE3Pi8HWUNMhmnCQwuEU6hA5Kho8wQXumEZAL8I5WhROfXN5sgAcKSUNHytAerKlrCD6HDcBKnZRB-RgFQLvdQlJ0hGwRp-dguhlMTZUvPuXIDYz4VTyt_NW9LSyFQDhj-Qoq0XxFSu1JapeMe2sfCZwoEbhg_-tPN9NUes4ZNKzZZIrXSRahQlgr5oxwoLpYgFHbxjtuQf6dhGYagKDFlCZ0MNYbKgJRChDTb7AnS9lqRmSvKOlXv7BLHCnGdwBiiqbwUOtNCUDDc5B4rRUeJv2OZI2zl-rXY43V7i85y6jxAdvMUsaRn_w.jpg

ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ፍተሻዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ወደ ከተማዋ በሚገቡ ዜጎች ላይ ፍተሻዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡

ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ይህም በተደራጀ መልኩ ጭምር የሚደረግ ነዉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች ከየትኛዉ አካባቢ በስፋት ወደ ከተመዋ እንደሚገቡ ያልገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤አበል እየተከፈላቸዉ ጭምር ከተመዋን ለመበጥበት የሚሰሩ አካላት መኖራቸዉን አንስተዋል፡፡

በተለይም የአደባባይ በዓላት ሲኖሩ ከፍተኛ የሰዉ ቁጥር ወደ ከተመዋ እንደሚገባ መንግስት መረጃ አለዉ ነዉ ያሉት፡፡

በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማን ሠላም ለማስጠበቅ ሲባል አጥፊዎችንና ሰላማዊ ዜጎችን ለመለየት ፍተሻዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የከተመዋ ነዋሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር የአዲስ አበባን ሰላም እንዲያስጠብቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

በአባቱ መረቀ

መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply