ወደ እስራኤል ለመሰደድ ሲጠባበቁ የነበሩ 3 ኢትዮጵያውያን በጎንደር ተገደሉ

ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በጎንደር ከተማ በታጣቂ ኃይሎች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር በተያያዘ በተተኮሰ ጥይት፤ ወደ እስራኤል ለመጓዝ ሲጠባበቁ የነበሩ 3 ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተገልጿል።

ተገድለዋል የተባሉት ሰዎች፣ “ፈላሽ ሙራ” ተብለው ከሚጠራው ቡድን ውስጥ ከሚገኙት በሺዎች ከሚቆጠሩ ስደተኞች መካከል መሆናቸውን ዘ ታይም ኦፍ እስራኤል ዘግቧል፡፡

ወደ እስራኤል ለመሄድ በጎንደር ከተማ በመጠባበቅ ላይ እያሉ የተገደሉት ሦስት ሰዎች፣ በታጣቂ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ጋር በተያያዘ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የቤተ እስራኤላዊያን ጉዞ አስተባበሪ ተናግረዋል፡፡

ግድያው ባለፈው ወር መጀመሪያ ላይ በጎንደር የተፈጸመ ሲሆን፤ ሰዎቹ የተገደሉት ሆን ተብሎ በተተኮሰ ጥይት ሳይሆን በተባራሪ ጥይት ነው ተብሏል፡፡

ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ፣ አንድ ወንድ ልጅን ጨምሮ ሌሎች ስድስት ወደ እስራኤል ሊሰደዱ የሚችሉ ስደተኞች ቆስለዋል ተብሏል፡፡

የሟቾቹ ሰዎች “ፈላሽ ሙራ” በመባል የሚታወቁት ማህበረሰብ አባላት ሲሆኑ፤ ወደ እስራኤል ለመሰደድ የሚያደርጉት ጥረት የበለጠ የተወሳሰበ እና ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ቤተ እስራኤል በመባል ከሚታወቁት በተለየ መልኩ የሚስተናገዱ መሆናቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

The post ወደ እስራኤል ለመሰደድ ሲጠባበቁ የነበሩ 3 ኢትዮጵያውያን በጎንደር ተገደሉ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply