ወጂዝ ሪል ስቴት በከፍተኛ የጥራት መመዘኛ የገነባቸውን 53 የአፓርታማ እና የንግድ ሱቅ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች አሰረከበ! በሪል ስቴት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኘው ወጂ…

ወጂዝ ሪል ስቴት በከፍተኛ የጥራት መመዘኛ የገነባቸውን 53 የአፓርታማ እና የንግድ ሱቅ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች አሰረከበ! በሪል ስቴት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኘው ወጂዝ ሪል ስቴት ፤ በታህሳስ 22 በሳፋየር አዲስ ሆቴል ባካሄደው የቤት ርክክብ ስነስርዓት ላይ ግንባታቸው የተጠናቀቀላቸውን (የዋና መግቢያ በር ፣ የመስኮት መስታወት እንዲሁም የመጨረሻ የቀለም ቅብ) ብቻ የቀሩት በቤተል አካባቢ (ሳይት-A) የሚገኙ በድምሩ 53 ባለ-ሶስት መኝታ አፖርታማ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን ለደንበኞች አሰረክቧል። በዝግጁቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የወጂዝ ሪል ስቴት የስራ ኃላፊዎች ፤ ወጂዝ ሪል ስቴት የአፖርታማ ቤቶቹን ግንባታ የጥራት ደረጃና የግንባታ ግብዐቶች አጠቃቀም በተመለከተ በከፍተኛ ትኩረት ሥራዎችን እንዳከናወነ ገልፀው ፤ “ደንበ…ኞች ራሳቸው ሊጨነቁበት በሚችለው መጠን ተጨንቀን ፣ ራሳችንን በደንበኞቻችን ቦታና ህልም ላይ አስቀምጠን ትውልድ ተሻጋሪ በሆነ የጥራት ደረጃ የአፖርታማ ቤቶቹን ግንባታ አጠናቀናል” ሲሉ ለዝግጅቱ ተዳሚዎች አስረድተዋል። የወጂዝ ሪል ስቴት ዋና መለያ የግንባታዎቹ የጥራት ከፍታ ላቀ ያለ መሆኑን ያስረዱት የወጂዝ የስራ ኃላፊዎች ፤ በመቀጠልም ሪል ስቴቱ በቅርቡ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ በሚገኙ ሌሎች ሳይቶቹ ለህጋዊና ውላቸውን በአግባቡ በመፈፀም ላይ ለሚገኙ ደንበኞቹ ቁልፍ የማስረከብ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በመኖሪያ አፖርትመንቶቹ ግንባታ ሂደት ወቅት በርካታ ደንበኞች በውል መሠረት በወቅቱ ክፍያቸውን ያለመፈፀምና ክፍያ የሟቀረጥ ክፍተቶች በመፍጠራቸው ምክንያት እንዲሁም በኮቪድ ወረርሺኝ ወቅት በተፈጠረው የስራ መቀዛቀዝ የርክክብ ጊዜውን በመጠኑ ቢያዘገየውም ወጂዝ ሪል ስቴት የነበሩትን አሰቸጋሪ መሰናክሎች ተሻግሮ ግንባታውን ከዳር ለማድረስ መብቃቱን አስታውሰው እዚህ ታላቅ ውጤት ላይ ለመድረስ ድጋፍ ያደረጉትን አካላት በሙሉ አመስግነዋል። በርክክቡ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ቁልፍ የተረከቡ ደንበኛ ሰይድ ሙሐመድ ” ወጂዝን ላመሰግነው እወዳለሁ፤ ብዙ መስዋዕትነት ከፍለዋል ፤ ሌት-ተቀን እየተገናኙ መፍትሄዎችን እያበጁ ከደንበኛው ጋር በተሻለ ቅርበት ሰርተው የቤት የባለቤትነት ህልማችንን እውን አድርገዋል:: አልሃምዱሊሏህ ሁላችሁንም ከልብ አናመሰግናለን” በማለት ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሌሎች ደንበኞችም ወጂዝ ሪል ስቴት ቃሉን ጠብቆ የቤት ባለቤት ስላደረጋቸው ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ቁልፍ የተረከቡ የወጂዝ ደንበኛ የሆኑት አቶ አህመድ ኢብራሂም በበኩላቸው “በሀገር ውስጥ ከተከሰተውና ከነበረው የዋጋ ግሽበት አንፃር በጣም ከፍተኛ ችግር እንዳይገጥማቸው የነበራቸውን ስጋት አስታውሰው ፤ በእውነት ቃል መግባት : ቃልንም መፈፀም እጅግ ከባድ ነገር ነው:: ወጂዝ ሪል ስቴት ይህን ስላሳካ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

Source: Link to the Post

Leave a Reply