ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃ.የ.ግ.ማ. ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመተባበር ”ወገን ፈንድ” የሚባል የኦንላይን የድጋፍ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ቴክኖሎጂው ጎፈንድ ሚ የሚተካ አገልግሎት ይሰጣል።በጎ አድራጊ ድርጅቶች በቀላሉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃ.የ.ግ.ማ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ቴክኖሎጂ ይዞ መጥቷል።በያዝነው ሳምንት አጋማሽ ላይ በይፋ ይተመረቀው ይሄው ቴክኖሎጂ በእንግሊዝ ሃገር ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር በላቸው ጨከነ እና አቶ ሚልዮን በተባሉ ኢትዮጵያውያን ትልቅ አስተዋጾ እንዳላቸው ለማውቅ ተችሏል።ቴክኖሎጂው ከአቢኒያ ባንክ ጋር በጋራ የሚሰራ ሲሆን በቴክኖሎጂው ይፋዊ መርሃግብር ላይ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።ከእዚህ በታች በአቢሲንያ ባንክ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ነው።======

Source: Link to the Post

Leave a Reply