“ወገን እየተራበ እኛ መጥገብ የለብንም!!!” ደራሲ እስማኤል ኃይለ ማርያም! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

“ወገን እየተራበ እኛ መጥገብ የለብንም!!!” ደራሲ እስማኤል ኃይለ ማርያም! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደራሲ እስማኤል ኃይለ ማርያም “የዋሻው ከተማ” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል። ደራሲው ከእዚህ ቀደም ያፈቀረው መናኝ፣ የስደተኛዋ ድምጽ እና ሁለቱ ጊዮርጊሶች የተሰኙ መጽሓፍቶችን ለሕዝብ ማድረሳቸው ይታወቃል። በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትንና አድናቆትን ያተረፉላቸው ስራዎቻቸው እንደሆኑ ደራሲ እስማኤል አስታውቀዋል። ጥቅምት 20 ቀን 2014 በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ በማንራ ሸዋ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ያስመረቁት መጽሐፉ የልቦለድ መጽሐፍ ሲሆን ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም በሙሉ ወሎ ላይ በርሃብና በጥም እንዲሁም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ላሉ ወገኖች የሚደርስ ስለመሆኑ ገልጸዋል። አክለውም አንባቢያን “የዋሻው ከተማ” መጽሐፍን ሲገዙ መቶ ብር ለወገናቸው እየረዱ እና እያነበቡ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። እንደ መጀመሪያ እቅድ የ 10,000 ሽህ ኮፒዎችን ሙሉ ገቢ ቃል የገቡ ሲሆን ከእዚህም ላይ የሚገኘው ገቢ ከአንድ ሚልዮን በላይ ይሆናል ነው ያሉት። ይህ ገቢ ለወገኖቸ ከደረሰ በኋላ የመጽሐፉ የሽያጭ ሂደት እየታዬ እስከ ሃምሳ ሽህ ኮፒና ከዚያ በላይም የምሰጥ ይሆናል ሲሉም ቃል ገብተዋል። መጽሐፉን በግልም በማህበርም በድርጅትም እየገዙ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጸሐይ ሐሩር እየተቃጠሉ፣ በብርድ ውርጭ እየተኮማተሩ፣ በርሃብ ጠኔ እየተጎሳቆሉ ላሉት ወገኖችዎ ይድረሱ ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በመጨረሻም ደራሲ እስማኤል “ወገን እየተራበ እኛ ጠግበን ማደር የለብንም! ቀን እስኪያልፍ ተካፍለን እንብላ!!!” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ምንጭ_ደራሲ እስማኤል ኃይለ ማርያም

Source: Link to the Post

Leave a Reply