You are currently viewing ወገኖቻችን እየታፈኑ ወደ እስር ቤት የተጋዙት በወንጀል በመጠርጠራቸው ሳይሆን በብልጽግና እና በህውሓት መሀከል በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ያደናቅፋሉ ተብለው በመጠርጠራቸው…

ወገኖቻችን እየታፈኑ ወደ እስር ቤት የተጋዙት በወንጀል በመጠርጠራቸው ሳይሆን በብልጽግና እና በህውሓት መሀከል በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ያደናቅፋሉ ተብለው በመጠርጠራቸው…

ወገኖቻችን እየታፈኑ ወደ እስር ቤት የተጋዙት በወንጀል በመጠርጠራቸው ሳይሆን በብልጽግና እና በህውሓት መሀከል በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ያደናቅፋሉ ተብለው በመጠርጠራቸው ነው›› ብለን በተናገርነው መሠረት ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ አምርተዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ነገ ደግሞ ኦቦሳንጆ በተቀመጡበት ሦፋ ላይ የብልጽግና መሪዎች ተቀምጠው ደብረ ጽዮን ጋር ሲተሻሹ ማየታችን አይቀርም፡፡ ያን ጊዜ ታዲያ ብ/ ጄኔራል ተፈራ ማሞን እና ምክትላቸውን ‹‹የወያኔ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች›› ብለው የወነጀሏቸው የብአዴን አመራሮች ‹‹ተዋረድን›› ብለው በመደበቅ ፈንታ ጌታቸው ረዳን በፍቅር ዐይን እየተመለከቱ ሲሽኮረመሙ ይታያሉ፡፡ ብልጽግና ላይ ትችት ሲሰነዝር ያዩትን ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሁሉ ‹‹በወያኔ ተላላኪነት›› እያጥላሉ ሆዳቸውን ሲሞሉ የከረሙ የገደል ማሚቶዎችም… አካውንታቸውን ዲአክቲቬት አድርገው በመሰወር ፈንታ ‹‹በወልቃይት ምድር ላይ ከህውሓት ጋር መዳራት ልክ አይደለም›› የሚሉ ድምጾችን ‹‹የኤርትራ ተላላኪዎች›› በሚል ፍረጃ እያጥላሉ ጅራታቸውን ሲቆሉ ይገኛሉ፡፡ ምንጭ:- አሳየ ደርቤ

Source: Link to the Post

Leave a Reply