ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት ከ1 ቢሊየን በላይ ብር ትርፍ ማሰመዝገቡን አስታወቀ።ባንኩ ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጉባኤን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።ባንኩ በበጀት አመቱ ከታክስ በፊት…

https://cdn4.telesco.pe/file/ak9F1RQXSp8waPaXr8Q9pNdMVEQlHmye9b1szJof-Jnimr9ymndDg2r2FMJ0w1_-UJ2EYXi1Hj-FMS6p_16d8IBCPRuRMGh2mS6NjvznPUwvFhh2pLnauQhtFy1ZX_1ztc3gov3xTGCfLEfRvMbBtBfI0p4o0LJ3fo4WTHrGxIm6tQXqncqXH9BqGVQ6BJ5TS32qNRtVfsCvreZFmTfFekfF9iQ-NKBQhiOJYZiBkWsx0rvXuvTXhkBD3P4UYGVwQMUs3sZ5Onh2_3kh3miMIwl86Z2BKXmOi2EEfPPsGEgKIIVPYvFPo_L8hDPEJqnRR2rJtNo2fNUujicpzKKUJA.jpg

ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት ከ1 ቢሊየን በላይ ብር ትርፍ ማሰመዝገቡን አስታወቀ።

ባንኩ ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጉባኤን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ባንኩ በበጀት አመቱ ከታክስ በፊት 1.1 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን የተገኘው ትርፍ ከዓምናው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 342 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው አስታውቋል።

በባንኩ ደንበኞች የተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ብዛትም የ38 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 1.8 ሚሊዮን መድርሱን የባንኩ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተፈራ ሞላ ተናግረዋል።

ባንኩ ለተለያዩ የብድር ዘርፎች ለደንበኞቹ የሰጠው አጠቃላይ የብድር መጠንም በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ 23.7 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ44 በመቶ ጭማሪ አስመዝግቧል።

በበጀት አመቱ በባንኩ የተከፈለ ካፒታል 2.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉም ወደ ብር 5.1 ቢሊዮን አድጓል።

እንደዚሁም የባንኩ አጣቃላይ ሀብት 38.2 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በሔኖክ ወ/ገብርዔል
ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply