You are currently viewing #ወጣት አበባው ማሙዬ በደብረብርሃን ከተማ መታፈኑ ተሰማ! ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ወጣት አበባው ማሙዬ ትውልድ እና እድገቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መረሃቢቴ አካ…

#ወጣት አበባው ማሙዬ በደብረብርሃን ከተማ መታፈኑ ተሰማ! ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ወጣት አበባው ማሙዬ ትውልድ እና እድገቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መረሃቢቴ አካ…

#ወጣት አበባው ማሙዬ በደብረብርሃን ከተማ መታፈኑ ተሰማ! ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ወጣት አበባው ማሙዬ ትውልድ እና እድገቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መረሃቢቴ አካባቢ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ የወረዳ ዘጠኝ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ባለሙያ ነው፡፡ ወጣት አበባው ማሙዬ ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄደበት ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ መታፈኑን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ በደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ጅሩ መንገድ አካባቢ ከወንድሙ ጋር ሲንቀሳቀስ ሲቪል የለበሱ እና በመከላከያ ፓትሮል መኪና የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ለጥያቄ እንፈልግሃለን ብለው እንደወሰዱት ቤተሰቦቹ ገልጠዋል፡፡ ከታፈነበት ሚያዚያ 30 ጀምሮ እስካሁን የት እንዳለ እንዳማያውቁ የገለፁት ቤተሰቦቹ በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል ጋዜጠኛ ጌራ ጌታቸው ገልጿል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply