You are currently viewing ወጣቶችን የፋኖ ስልጠና አትወስዱም ብሎ ማሰሩ መቆም አለበት!! ባህርዳር :- የካቲት 10/2014  ዓ.ም                  አሻራ ሚዲያ ከወጣቶች ጋር ተግባብቶ መስራት እንጅ ወጣት…

ወጣቶችን የፋኖ ስልጠና አትወስዱም ብሎ ማሰሩ መቆም አለበት!! ባህርዳር :- የካቲት 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከወጣቶች ጋር ተግባብቶ መስራት እንጅ ወጣት…

ወጣቶችን የፋኖ ስልጠና አትወስዱም ብሎ ማሰሩ መቆም አለበት!! ባህርዳር :- የካቲት 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከወጣቶች ጋር ተግባብቶ መስራት እንጅ ወጣት ጥያቄ ባነሳ ቁጥር ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ ማሰር መቆም አለበት !!!… በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖዎች ወጣቶችን በማደራጀት ወደ ፋኖ እንዲቀላቀሉ በቅን ልቦና ስልጠና የሚሰጡ ወጣቶችን በማሠር የሚመጣ ለውጥ የለም። በሰሜን ሸዋ አቡሽ ጌታቸው አደራን የአብን የሚዳ ወረሞ አስተባባበሪ ነው። ብአዴን አስሮታል። አቡሽ ጌታቸው የሚገርም እይታ አለው። ወያኔ አማራን እንደሚወር ቀድሞ የገባውና ሙሉ ወረራ እንደሚያካሂድ ወጣቶችን ፣ በተለይ በወረኢሉና በጃማ ጥንቃቄ መደረግ አለበት በማለት ሲያነቃቃ ነበር። አበበ አላዩም ተመሳሳይ ብቃት ያለው ወጣት የህክምና ባለሙያ ነው። እንግዳሸት ጸደቀ፣ አበበ አላዩ፣ አቡሽ ጌታቸውና ሌሎችም ቀደም ካለው ጊዜ አንስቶ ብአዴንን ሲቃወሙ ሰው ሲዘባበትባቸው ነበር። አሁን እነዚህ ወጣቶች እስርቤት ቤት ናቸው። ማዕከላዊ መንግስት እነ ታምራት ላይኔን ተንከባክበው እነ ታምራት ነገራን ያስራሉ፣ ታች አደረጃጀት ላይ ያሉት ደግሞ እነ አበበንና አቡሽን ያስራሉ። በተመሣሣይ ሠጃን መላኩ ክንዴ ተደብቆ የቆየ የእሥር ጉዳይ ነው ። ከኢመደቨኛ ፍኖ ጋር እንቅሥቃሤ አድርግሀል በሚል ታስሯል። ሠጃን በበረሀ ከባድ መሥዋት ሢከፍልና አሁንም በነበረው ሀገራዊና ወቅታዊ ህግ የማሥከበር ዘመቻ ላይ ትልቅ ጀብድ በሶሮቃ ቅራቅር እሥከ ተከዜ ድንበር የከፈለው መሥዋትነተ ሊያሸልመው ሢገባ ለምን ከፍኖ ጋር ታየህ ተብሎ ያለምንም የጊዜ ቀጠሮ በባህርዳር ማረሚያ ቤት ውስጥ 3 ወር ሙሉ ያለምንም የጊዜ ቀጠሮ ታስሮ ይገኛል ። እሥካሁን ባየር ላይ ታፍኖ ቁጭ ያለው እና ድምፅ ሁኑት ብለው ቤተሰቦቹ ተማፅነዋል። ትኩረት ለአማራ ፋኖወች!! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply