ወጣቶች አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድንን በመደምሰስ የጀግኖች አባቶችን አኩሪ ታሪክ ሊደግሙ እንደሚገባ የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ጥሪ አቀረበ፡፡ ጥቅምት…

ወጣቶች አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድንን በመደምሰስ የጀግኖች አባቶችን አኩሪ ታሪክ ሊደግሙ እንደሚገባ የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ጥሪ አቀረበ፡፡ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ) የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ለህልውናው ዘመቻ ከ100 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፉ ሥነሥርዓት ላይ የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀመንበር ዳኝነት አያሌው አባቶች ሀገራቸው በየወቅቱ የሚገጥማትን ጠላት በዘር፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ ሳይከፋፈሉ እርስ በርሳቸዉ በመዋደድ ሲደመስሱ እንደነበር አስታውሰዋል። አባቶች ሀገራቸውን የሚወር ጠላት በመጣባቸዉ ጊዜ ሁሉ እንደብረት አንድነታቸዉን አጠናክረው ቀፎው እንደተነካበት የንብ መንጋ “ሆ!” ብለው የሀገራቸውን ሉዓላዊ…ነት በማስከበር ለትውልድ እንዳስረከቡ አስረድተዋል። አባቶች የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጠብቀዉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረዉ ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ ለአሁኑ ትዉልድ በክብር አስረክበዋል ነው ያሉት። አሁንም ቢሆን ወጣቱ ተመሳሳይ ታሪክ ሊደግም እንደሚገባ ያሳሰቡት ሊቀመንበሩ ኅብረተሰቡ በተለይ ወጣቱ የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የህልውና ዘመቻውን ሊቀላቀል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። አሸባሪው ትህነግ አማራ ጠላቴ ነዉ ሒሳብ አወራርዳለሁ፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል እገባለሁ ብሎ በመነሳት የአማራና የአፋር ክልሎችን በመውረር የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ፣ እያፈናቀለ፣ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች የመንግሥትና የግል ተቋማትን እያወደመ እንደሚገኝ አስረድተዋል። አረመኔውን የጥፋት ቡድን ለመደምሰስ ብሎም እስከመጨረሻዉ የሰላምና ጸጥታ ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በግንባር ተሰልፈዉ ጠላትን ለመፋለም እያደረጉ ያሉትን ትግል የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት በአድናቆት ያዩታል ነው ያሉት። የአማራ ክልል ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባል ሻምበል ባሻ የኔው አባቶች ምንም አይነት ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ሳይኖራቸው የሀገርን ዳር ድንበር አስከብረዋል ብለዋል። አሁን ላይ ወራሪው የትህነግ ቡድን በምድር ላይ የማይተገበር ግፍ በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ይገኛልም ነው ያሉት። ወጣቱ አንድነቱን ጠብቆ የዚህን አረመኔ ቡድን ሴራ ማክሸፍ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል። ወጣቱ ጠላትን ከመደምሰስ በተጨማሪ ድህነትን አጥብቆ መታገል እንደሚኖርበት አስረድተዋል። የፋግታ ለኮማ ወረዳ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀመንበር ታደለ ነጋሽ ጠላት በቆፈረው ምሽግ ውስጥ ራሱ እንዲቀበር ወጣቱ የአባቱን ታሪክ መድገም እንዳለበት ገልጸዋል። ጥንታዊ አርበኞችም ቢሆኑ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ እስከ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። ሕዝቡ የመንግሥትን ጥሪ ተቀብሎ ሀገሩን ከመደፈር መታደግ አለበት ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን በ17 ወረዳዎች የሚገኙ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበራር አባላት ለህልውናው ዘመቻ የሚውል ከ100 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶክተር) ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። ዶክተር ጥላሁን የማኅበራቱ ድጋፍ ኅብረተሰቡ ለህልውናው ዘመቻ ድጋፍ እንዲያደርግ አርዓያ ይሆናልም ነው ያሉት። ኀላፊው እንዳሉት ወራሪውን ቡድን ለመመከት ከወገን ኀይል ተጋድሎ በተጨማሪ ሕዝቡ በጉልበትና በዕውቅት ድጋፍ እያደረገ ሲል አሚኮ ዘግቧል። አሻራሚዲያ – የአይበገሬዎቹልሳን!!! ለፈጣንናአዳዲስመረጃዎችየአይበገሬዎቹልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :- https://t.me/asharamedia24 Youtube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply