ወጣቶች ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ ወታራዊ ማሰልጠኛ በረሃማ ካምፖች እየተወሰዱ ነው። ለንደን :- ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከማሰልጠኛዎች…

ወጣቶች ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ ወታራዊ ማሰልጠኛ በረሃማ ካምፖች እየተወሰዱ ነው። ለንደን :- ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከማሰልጠኛዎች መካከል ኦጋዴን፤ ጎዴ አንዱ ነው። በዚህ ማዕከል በምሽት ሲንቀሳቀሱ በመንገድ ላይ ድንገት እየታፈሱ ተወስደው ለልዩ ኦፕሬሽን በሚል በግዳጅ ውትድርና እየሰለጠኑ ከሚገኙት መካከል ሕፃናት፣ ህሙማን እና አካል ጉዳተኞች ይገኙበታል። ደብዛቸው ከጠፋ ከ12 ቀናት በኋላ በደብረ ዘይት ታግተው የተገኙ ወጣቶቾም አሉ። እነዚህ ወጤቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በነፍስ ወከፍ 10 ሺህ ብር ለጠባቂዎች ከፍለው እንዲወጡም ተጠይቀዋል። እንደ መረጃ ምንጮች ገለፃ አብዛኞቹ የሚከፈል ገንዘብ ስለሌላቸው አብዛኞቹ አሁንም በእገታ ላይ ናቸው። ከታገቱ ወጣቶች መካከል የሚከተሉት አማሮች ይጠቀሳሉ፦ 1ኛ. ቻሌ ገነት 2ኛ.መዝገብ አወቀ 3ኛ. ስለሽ ጌታነህ 4ኛ. መልካሙ ዋለ 5ኛ. ይበሉ ታደስ 6ኛ. ገነቱ ቻሌ 7ኛ. አዲሱ ተፈራ 8ኛ. ምስጋነው ተፉራ 9ኛ. ዘመኑ በላይነህ 10ኛ. ሞላልኝ አቡታ 11ኛ. አዲሱ ትላሁን 12ኛ. እያሱ ሙለታ 13ኛ. ድረስ (የአባቱን ስም አላረጋገጥኩም) 14ኛ. በልያውቃል አማረ እነኝህ ወጣቶች ከአዲስ አበባ ተወስደው ጅግጅጋ አንድ ቀን ካደሩ በኋላ ወደ ጎዴ የተወሰዱ ናቸው። በስም ያልታወቁ ሌሎች ሦስት ወጣቶችም አብረዋቸው ይገኛሉ። ©ጌጥዬ ያለው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply