ወ/ሮ ቀለብ ስዩም የህክምና መብቷ ተከለከለ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ፡፡                 አሻራ ሚዲያ          ህዳ…

ወ/ሮ ቀለብ ስዩም የህክምና መብቷ ተከለከለ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳ…

ወ/ሮ ቀለብ ስዩም የህክምና መብቷ ተከለከለ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-16/03/13/ዓ.ም ባህርዳር በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት ወ/ሮ ቀለብ ስዩም በጀርባ አንጥት ህመም ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገልጻል፡፡ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም በሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው ቃሊቲ እስር ቤት እንደሚገኙ ገልጾ በሀሰት የሽብር ወንጀል መከሰሳቸው አልበቃ ብሎ ለህመማቸው የተሸለ ህክምና እንዳያገኙ ተደርገዋል ብሏል፡፡ በጀርባ አንጥት ህመም የሚሰቃዩት ወ/ሮ ቀለብ ስዩም የተሸለ ህክምና አግኝተው ከህመማቸው እንዲድኑ ማረሚያ ቤቱን ቢጠይቁም ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በከፍተኛ የጀርባ ህመም ሌት ተቀን እየተሰቃዩ መሆናቸውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል፡፡ እንድ ዜጋ ህክምና የማግኘት መብቱ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሊጠበቅለት እንደሚገባ በህግ የተደነገገ ቢሆንም የወ/ሮ ቀለብ ስዩም ግን ይህ መብታቸው ተነፍጓል ብሏል ፓርቲያቸው፡፡ ስለሆነም ህመማቸው ከቀን ወደ ቀን እየበረታ የመጣ ስለሆነና ከፍተኛ ችግር ስለገጠማቸው ፓርቲው ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ይህንን ችግር ተረድቶ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ህክምና የማግኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው የበኩሉን ትግል እንዲያደርግ በትህትና እንጠይቃለን ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ዘጋቢ፡ -ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply