ወ/ሮ አዳነች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦምብ የሶስት የጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

ወ/ሮ አዳነች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦምብ የሶስት የጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦምብ የሶስት የጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ምክትል ከንቲባው በፈነዳው የእጅ ቦምብ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ በጣም አዝነናል ብለዋል ።

ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ቦምቡ ፈንድቶ ጉዳት ማድረሱ የሚታወስ ነው።

The post ወ/ሮ አዳነች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦምብ የሶስት የጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply