ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስአ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ˝በከተማችን፣በሀገራችን እና በመላው ዓለም የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም እንኳን ለገና “˝ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል˝” በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለዉ ብለዋል።

በተለይም በዚህ ከቤተሰብ፤ ከወዳጅ ዘመድ  ጋር  በአብሮነት፤ በጨዋታ በሚከበር በአል ላይ በስራ ገበታችሁ ሆነው ለሚያከብሩ የክርስትና እምነት ተከታይ   ለሆኑ ኢትዮጵያውያን፤ ትውልደ ኢትዮጵውያንና  መልካም የገና በአል ሲሉ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልዋል።

በተመሳሳይ የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ የገናን በዓል ሲያከብር ለዘመናት የዘለቀውን የመደጋገፍ ባሕል እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነችና ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ በአሉን ሲያከበብር አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የኮቪድ -19 ወረርሺኝ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply