
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሠጣጥን ተዘዋውረው ጎበኙ።
አመራሮቹ ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን፣ ታክሲ አሽከርካሪዎችን፣ ተራ አስከባሪዎች እና የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎችን አነጋግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ችግርን ለመቅረፍ ከአውቶቡስ አቅርቦት ጀምሮ የመሰረተ ልማት እና የትራፊክ ማኔጅመንት ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሠጣጥን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post