ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ማዕድ አጋሩ

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 1 ሺህ 495ኛውን የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን (መውሊድ) ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን በዛሬው ማዕድ አጋርተዋል።

ጎዳና ተዳዳሪዎቹን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ከሆኑት አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እና የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ መግበዋል።

ወይዘሮ አዳነች በዓልን ስናከብር በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ ያሉ ዜጎችን በማሰብ መሆን አለበት ብለዋል።

ምክትል ከንቲባዋ አያይዘውም መላው የከተማዋ ነዋሪዎች እነዚህን ዜጎች በሚችለው አቅሙ በማገዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ማዕድ አጋሩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply