ዊጋን ቱሬን ሾመ!

ዊጋን አትሌቲክ የቀድሞውን የአርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ አዲሱ አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል ፡፡

የኮሎ ቱሬ ኮንትራት ለሶስት ዓመት ከስድስት ወር የሚዘልቅ እንደሆነም ተነግሯል ፡፡

የ41 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊ ኃላፊነቱን የተረከበው ሊያም ሪቻርድሰንን ተክቶ ነው ፡፡ የሻምፒየንሺፑ ክለብ የቀድሞውን አሰልጣኝ ያሰናበተው በዚህ ወር መጀመሪያ እንነበር ይታወሳል ፡፡

ቱሬ ያለፉትን አምስት ዓመታት በብሬንዳን ሮጀርስ ስር በሴልቲክ እና ሌስተር ሲቲ ሰርቷል፡፡ በኃላፊነት የሚረከበው የመጀመሪያ ስራውም ሆኗል ፡፡

ዊጋን በታህሳስ መጀመሪያ ከሜዳው ውጪ ሚልዎልን ሲገጥም ቱሬ በዋና አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ጨዋታውን ይመራል፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply