ዌስት ባንክ ውስጥ ሦስት ፍልስጥዔማዊያን ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/01630000-0aff-0242-7803-08da79f84d59_w800_h450.jpg

ዌስት ባንክ ውስጥ የእሥራኤል ወታደሮች ሦስት ፍልስጤማውያንን ተኩሰው መግደላቸውን የፍልስጥዔም የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። 

የእሥራኤል ባለሥልጣናት ደግሞ ናብሉስ ከተማ ውስጥ ሰዎችን ለመያዝ ዛሬ በተደረገ እንቅስቃሴ ወቅት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ወታደሮቻቸው ሁለት ፍልስጥዔማዊያን ታጣቂዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

ግጭቱ የተከሰተው በእስራኤልና በፍስልስጥዔሙ እስላማዊ ጂሃድ መካከል ለሦስት ቀናት የዘለቀውን ውጊያ ያቆመው ስምምነት ከተደረሰ አንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው። 

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ዜጎቿን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ጥቃቶች መካሄዳቸውን ተከትሎ እሥራኤል ባለፉት ወራት ዌስት ባንክ ውስጥ በየምሽቱ በሚባል ሁኔታ ፍስልጥዔማዊያን ታጣቂ ቡድኖችን በመውረር በቁጥጥር ሥር የማድረግ ዘመቻ ስታካሄድ መቆየቷን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply