#ውቢቷ ባህርዳር የባለዘንባባዋ ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ አጭር ታሪክ▭ በ14ኛው ክ/ዘመን የተመሰረተችው የባህር ዳር ከተማ አሁን ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከሚገኝበት ቦ…

#ውቢቷ ባህርዳር የባለዘንባባዋ ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ አጭር ታሪክ▭ በ14ኛው ክ/ዘመን የተመሰረተችው የባህር ዳር ከተማ አሁን ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከሚገኝበት ቦታ ላይ የኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በመመስረቷ በመንደርነት ተቆረቆረች። በ1928 ዓ.ም ካህናት ባላባት እና እስላም የተባሉ 3 መንደሮች ሆኑ በ1929 ዓ.ም በአዲስ የከተማ ፕላን በዘመናዊ አስተዳደር መመራት ጀመረች፡፡ በ1935 ዓ.ም በወረዳ ከተማነት በ1937 ዓ.ም ደግሞ በማዘጋጃ ቤት መመራት ጀመረች፡፡ በ1948 ዓ.ም የባህር ዳር ከተማ አውራጃ ሆነች በ1985 ዓ.ም የአብክመ ዋና ከተማ ሆነች፡፡ ባሕር ዳር ከተማን ከአስተዳዳሪነት እስከ ከንቲባነት የአስተዳደሩ ❶ ደጃዝማች ጊላ ወልደጊዮርጊስ ከ1934-1936ዓ.ም ❷ ባላምባራስ ወርቅነህ ካሳ ከ1936-1944ዓ.ም ❸ መዝገቡ ጥበቡ ከ1947-1955ዓ.ም ❹ ፈትአውራሪ ሀ/ማርያም ወ/ኪዳን ከ11955-1963ዓ.ም ❺ አቶ በላይ ከበደ ከ1970-1973ዓ.ም ❻ መቶ አለቃ አባይነህ ኢሳ ከ1973-1978ዓ.ም ❼ አቶ ወርቁ መርሻ ከ1978-1983ዓ.ም ❽ አቶ በቀለ አንለይ ከ1983-1984ዓ.ም ❾ አቶ ንብረቱ ገነቱ ከ1984-1985ዓ.ም ❿ አቶ ደባሱ መንግስቱ ከ1985-1986ዓ.ም ⓫ አቶ ገዙ እሸቱ ከ1986-1988ዓ.ም ⓬ አቶ አውላቸው ውቤ ከ1988-1989ዓ.ም ⓭ አቶ ቀራለም ሳልለው ከ1990-1993ዓ.ም ⓮ አቶ ተፈራ ታዲዮስ ከ1993-1994ዓ.ም ⓰ አቶ ጌታሁን ብርሃኑ ከ1994-1996ዓ.ም ⓱ አቶ ማርየ ከፍያለው ከ1996-1997ዓ.ም ⓲ አቶ ያየህ አዲስ ከ1997-1999ዓ.ም ⓳ አቶ አለማየሁ ሰዋገኝ ከ1999-2002ዓ.ም ⓴ አቶ ስማቸው ወንድማገኝ ከ2002 -2005ዓ.ም ❷➊ አቶ ላቀ አያሌው ከ2006-2009 ዓ.ም ➋➋ አቶ አየነው በላይ ከ 2009-2011ዓ.ም ➋➌ አቶ ሙሉቀን አየሁ ከ2011-2012 ዓ.ም ➋➍ መሃሪ ታደሰ ( PHD) 2012 ዓ.ም ➋➎ ድረስ ሳህሉ(PHD) ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ – — ይምጡ ውቢቷን ባሕር ዳር ከተማን ይጎብኙ❗️

Source: Link to the Post

Leave a Reply