ውጥረት ውስጥ የሚገኙት የሩዋንዳ እና ኮንጎ ሪፕብሊክ መሪዎች ፍትለፊት ሊገናኙ ነው፡፡

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና የኮንጎ ሪፕብሊክ ፕሬዝዳንት ፍክሲ ቴሺዳ በመሃከላቸው ስላለው ውጥረት ለመሀመርያ ጊዜ ፍትለፊት ተገናኝተው ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማረገብ በአፍሪካ ህብረት የተወከሉት የአንጎላው ፕሬዝዳንት ጃኦ ሎሬንኮ አደራዳሪነት ሁለቱ ሀገራት ሊመክሩ መሆኑ ነው አፍሪካ ኒውስ ያወጣው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

ለሁለቱ ሀገራት የግጭት ምክንያት የሆነው ኤም23 የተሰኝው አሸባሬ ቡድን መሆኑ ይነገራል፡፡

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ትጥቅ አንግበው መዋጋት ከጀመሩ አሥር ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት የኤም 23 ተዋጊዎች፣ ዘንድሮ ከጥቅምት ወዲህ ዳግም ተጠናክረው በከፈቱት ጥቃት በርካቶችን እየገደሉና እያፈናቀሉ ነው፡፡

በአብዛኛው የኮንጎ ቱትሲ ጎሳ አባላት ናቸው የሚባሉት የኤም 23 ተዋጊዎች ከዓመታት ዝምታ በኋላ በፈረንጆቹ በ2021 ላይ አንዳንድ የኮንጎ ምሥራቃዊ ከተማዎችን መቆጣጠር ቢጀምርም፣ ከአገሪቱ መንግሥት ጋር ከባድ ጦርነት ውስጥ ከገባ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ኮንጎ ሪፕብሊክ ሩዋንዳ በሃገራችን የውክልና ጦርነት እያካሄደች ነው ስትልም ትከሳለች፡፡
የኤም 23 ታጣቂ ቡድን ጦርነቱን እኛ አልጀመርንም፣ የጀመሩት የኮንጎ ወታደሮች ናቸው ኃላፊነት አንወስድም፤ ቢሉም፣ ተመድን ጨመሮ ሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊዎች ኤም 23 እና ሩዋንዳን ይወነጅላሉ፡፡

ይህንን ውጥረት ለማርግብ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ አሜሪካ እና የመንግስታቱ ድርጅት የተለያዩ የማግባባት ስራ ቢሰሩም እስካሁን የተገኝ ውጤት የለም፡፡

ሁለቱን ሀገራት እንዲያግባቡ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የተሸሙት የአንጎላው ፕሬዝዳንት ጃኦ ሎሬንኮ ውጤት ያመጣሉ በሚል ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply