You are currently viewing “ዐማራ ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ተጠያቂው የብልፅግና መንግሥት ነው!” ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…    ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ….

“ዐማራ ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ተጠያቂው የብልፅግና መንግሥት ነው!” ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ….

“ዐማራ ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ተጠያቂው የብልፅግና መንግሥት ነው!” ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ፣ ከ 1000 በላይ እንደሚሆኑ የሚገመት ንጹሃን የዐማራ እናቶች፣ ህፃናትና፣ አዛውንቶች፣ በኦሮሞ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። ከሞት የተረፉትና የአካልና የስነልቦና ጉዳት የደረሰባቸው ከ 10000 (አስር ሺ) በላይ የዐማራ ተወላጆች አሁንም በጫካ ተበታትነው ይገኛሉ። እነዚህ መከራ የተደፋባቸው የዐማራ ተወላጆች፣የእኔ የሚሏቸውን የቅርብ ሰዎች ተነጥቀው፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ፣ ያለምንም መጠለያና ረዳት በፍርሀትና በሀዘን ተቆራምደው በጭንቅ ላይ ናቸው። ዐማራን ቤት ለቤት አሳደው የጨፈጨፉትና ያቃጠሉት ገዳዮቹ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው። ይኸንንም ማረጋገጥ የተቻለው ራሳቸው በእብሪት በሚለቁት አሰቃቂ ቪዲዮ ጭምር ነው። የብልፅግናው መንግሥት እንደለመደው የዘር ጭፍጨፋውን ቀለል አድርጎ እንደተራ ዜና “በኦነግ ሸኔ” ተፈጸመ፤ ብሎ ሲከስ፣ ኦነግ ሽኔ ደግሞ በአንጻሩ ጭፍጨፋዉ የተፈጸመዉ በመንግሥት ታጣቂዎች ነው፤ የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከሰለባው የወለጋ ነዋሪ የዐማራ ህዝብ ባገኘው መረጃ፣ ገዳዮቹ ዐማራ ጠል የዘር ፖለቲካ አራማጅ የኦሮሞ ታጣቂዎች በተቀናጀ መልኩ፣ ተናበው እንደሚሰሩ አረጋግጧል። አገዛዙ “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው ትጥቅ የሌላቸውን ንፁሀን የዐማራ ተወላጆችን የሚፈጁት ሙሉ የወታደር ትጥቅና ስንቅ ቀርቦላቸው ነው። ገዳዮቹ እንዴትና ማንን መግደል እንዳለባቸው በዚህ በያዝነው ሰኔ ወር ብቻ በፓርላማ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድና በሚኖሶታ/አሜሪካ የኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ በአቶ በቀለ ገርባ የተነገረውን ጥላቻና ወደዘር ማጥፋት የሚወስድ ቅስቀሳን በቀጥታ ተርጉመው በተግባር እንዳዋሉት ብዙዎች ይመሰክራሉ። አስተዛዛቢው ደግሞ የአገዛዙ የብልፅግና መንግሥት ባለስልጣናት ጠቅላይ ሚንስትሩንና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥን ጨምሮ የዐማራ ህዝብ እያለቀ፣ እንደመሪም ሆነ እንደባህላችን የንፁሀንን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከምንም ሳይቆጥሩ፤ አትክልት ቦታ ሲጎበኙ እንደነበር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለህዝብ ይተላለፍ ነበር። ይባስ ብለውም የዐማራ ህዝብ ደም እንደጅረት ውሀ ሲፈስ፤ የሞቱት አፈር ሳይለብሱ፤ ቆስለው የወዳደቁት ሳይነሱ፤ የተጨነቁትን የማዳን ስራ ሳይሰራ፤ በሚቀጥለው ሰኔ 13 ቀንም እንዲሁ “አረንጓዴ አሻራ” በሚል መፈክር ችግኝ ሲተክሉ በቴሌቪዥን ሲታዩ ዋሉ። የንጹሃኑ እልቂት የችግኙን ሩብ ያህል የሚዲያ ሽፋን አለማግኘቱና አረንጓዴ አሻራ ያሉት የችግኝ ተከላ “ከንጹሃን የደም አሻራ” ጋር ሲወዳደር ሚዛን ስለማይደፋ አገዛዙ የዐማራ ሕዝብ ፍጅት ተባባሪ እንደሆነ አስመስክረዋል። አሳሳቢው ነገር ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ የጥላቻና ወደ ዘር ማጥፋት የሚወስድ ቅስቀሳና የአቶ በቀለ ገርባ ኢትዮጵያን የማጥፋት እቅድ፣ በቀጣይ በወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሻሸመኔ በመሳሰሉት የተጀመረው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሀል አዲስ አበባም እንደማይገባ ማረጋገጥ ስለማይቻል ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብናል። በተለይ በዐማራ ክልል ኮሽ ባለ ቁጥር በማጋነን “ሙስሊም ተበደለ” እያሉ በመጮህና ቅስቀሳ በማድረግ በርካታ ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉና የዐማራ ህዝብ በሀይማኖት ስም እንዲጨራረስ የሚያደርጉት ጎጠኛ የኦሮሞ ፅንፈኛ ኡስታዞች በመስጊድ የተጠለሉትን ሳይቀር ሙስሊም የዐማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ፍጅት አለማውገዛቸው ለዐማራ ሕዝብ የተደገሰለትን የሞት ፅዋ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የመንግሥት አስፈላጊነትና ዋነኛ ተግባር የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ማክበርና ማስከበር ቢሆንም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በለውጥ ስም የኦሮሙማው አገዛዝ ይህን ሲያደርግ አላየም። ድርጅታችን አገዛዙ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በተደጋጋሚ በዐማራ ዘር ላይ ያተኮረውን የዘር ጭፍጨፋ በመቃወም ባወጣው መግለጫ፤ አገዛዙ የንጹሀንን ግድያ እንዲያስቆም፣ ተደጋጋሚው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና ወንጀለኞቹን ተጠያቂ እንዲያደርግ፤ ግድያውን እውቅና ሰጥቶ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብና በግፍ የተጨፈጨፉት እንዲታወሱ እንዲያደርግ ሲያሳስብ ቆይቷል። የአሁኑን የወለጋ ጭፍጨፋ የተለያዩ በውጪ አገር ያሉ አለም አቀፍ የሚዲያ አውታሮች ዘገባና አሜሪካና ኢራንን ጨምሮ አንዳንድ መንግሥታት ባወጡት መግለጫ “ጭፍጨፋው ዘር ተኮርና በዐማራ ተወላጅ ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት እንደሆነ” አሳይተዋል። በአንፃሩ የኢትዮዽያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የኢትዮዽያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ፣ እንደ ብልፅግናው መንግሥት ሁሉ እውነታውን በመሸፋፈን፣ በወለጋ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ ባወጡት መግለጫ “በሲቪሎች ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው” በማለት ለማድበስበስ መሞከራቸው ክፉኛ አሳዝኖናል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በኢትዮጵያ ውስጥ ሲፈፀም የኖረውንና የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እያወቀ እንዳላወቀ በቸልተኝነት ማለፉ ከተጠያቂነት አያድነውም። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ዛሬ በዐማራ ላይ ብቻ ያነጣጠረው የዘር ማጥፋት ነገ በሌሎቹ ነገዶች ላይ እንደሚዛመት ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። ይህ ወንጀል እንደሰደድ እሳት ተስፋፍቶ ሕዝብ ከሕዝብ ጋር ከመተላለቁ በፊት:_ 1) ትግል ከቤት ይጀመራልና፣ ከኦሮሙማ አገዛዝ ጋር ተባብሮ የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል “ፋኖ” ን የሚያሳድደውን፣ የዐማራ ህዝብ ደም ሲፈስ ለገዳይ ካባ በማልበስ የሚታወቀውን አዴፓ/ብአዴንን የአማራ ወጣት በማንኛውም የህዝባዊ እንቢተኝነት መንገድ በመቃወም ጥፋት የታወጀበትን ወገኑን በመታደግ ራሱን ከአደጋ እንዲከላከል፤ 2) ታሪክ እንደሚያሳየው መንግሥት ይመጣል ይሄዳል። አብሮ የሚኖረው ደግሞ ህዝቡ ነው። ስለዚህ መላው ሀገር ወዳድ የኦሮሞ ሕዝብ፣ለዐማራው ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለእራሱም ሰላምና ደህንነት ሲል በስሙ የሚነግዱ የፖለቲካ ነጋዴዎችንና ጨፍጫፊዎችን በማውገዝ ተቃውሞውን እንዲያሰማና ብልፅግናን ተጠያቂ እንዲያደርግ፣ 3) የተባበሩት መንግሥታት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ቀይ መስቀል፣ እና የመሳሰሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ወንጀሉን በማውገዝ ከተበዳይ ጎን እንዲቆሙና የወደፊት አደጋን ለማስቆም እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply