You are currently viewing ዐቃቢ ህግ በባህር ዳር እስር ቤት ባሉ እና በተፈቱ የጦር መኮንኖች ላይ ያቀረበው የይግባኝ መዝገብ ለውሳኔ በሚል ለፊታችን የካቲት 17 ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 24…

ዐቃቢ ህግ በባህር ዳር እስር ቤት ባሉ እና በተፈቱ የጦር መኮንኖች ላይ ያቀረበው የይግባኝ መዝገብ ለውሳኔ በሚል ለፊታችን የካቲት 17 ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 24…

ዐቃቢ ህግ በባህር ዳር እስር ቤት ባሉ እና በተፈቱ የጦር መኮንኖች ላይ ያቀረበው የይግባኝ መዝገብ ለውሳኔ በሚል ለፊታችን የካቲት 17 ተቀጥሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ በባህር ዳር ሰባታሚት እስር ቤት ባሉ እና በተፈቱ ስለሽ ከበደን ጨምሮ በአራት የጦር መኮንኖች ላይ ያቀረበው የይግባኝ መዝገብ ለውሳኔ በሚል ለፊታችን የካቲት 17/2015 ተቀጥሯል። ይህ የዐቃቢ ህግ የይግባኝ መዝገብ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በሚል ለጥር 19/2015 ተቀጥሮ እንደነበር ታውቋል። ከአሁን ቀደም በነጻ የተሰናበቱት አራት ሰዎች አልቀረቡም በሚል በጋዜጣ ስማቸው ተጠቅሶ ጥሪ ከተደረገ በኋላ በሌሉበት ይታይ ስለመባሉ ተሰምቷል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ያሉ የጦር መኮንኖች በፕላዝማ እየቀረቡ ሂደቱ ይከታተሉ የነበር ቢሆንም ጥር 19/2015 ግን ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ አለመቅረባቸው ተገልጧል። ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ 2ኛ ወንጀል ችሎት መሆኑ ይታወቃል። ሰኔ 15/2011 ከተፈጸመው ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በተከፈተው መዝገብ 35 ተከሳሾች መካተታቸው እና ከመካከላቸውም 4ቱ በሌሉበት፣ 31 የሚሆኑት ደግሞ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር መቆየታቸው በሂደቱም ሌሎች ሲፈረድባቸው 4 የሚሆኑት በነጻ ከእስር መሰናበታቸው ይታወሳል። ዐቃቢ ህግ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ አንሷል በማለት ይግባኝ መጠየቁ እና ይግባኙም ጉዳዩ በቀረበለት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ 2ተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ የክርክር ሂደቱ መቀጠሉም አይዘነጋም። ይህ የይግባኝ የክርክር መዝገብም ለውሳኔ በሚል ለጥር 19/2015 ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ችሎቱ ውሳኔ ለማሳረፍ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ እንደገና ለየካቲት 17/2015 መቀጠሩን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ጠበቃ ጎሽይራድ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply