You are currently viewing ዐቃቢ ህግ በጋዜጠኛ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ ላይ ተደራራቢ ክስ መስርቷል፤ በዋስትና እና ሌሎች የመብት ጉዳዮች ላይ የተነሱ አቤቱታዎችን ለመስማት በሚል ፍ/ቤቱ ለፊታችን ሰኞ ጠዋት እንዲቀርቡ…

ዐቃቢ ህግ በጋዜጠኛ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ ላይ ተደራራቢ ክስ መስርቷል፤ በዋስትና እና ሌሎች የመብት ጉዳዮች ላይ የተነሱ አቤቱታዎችን ለመስማት በሚል ፍ/ቤቱ ለፊታችን ሰኞ ጠዋት እንዲቀርቡ…

ዐቃቢ ህግ በጋዜጠኛ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ ላይ ተደራራቢ ክስ መስርቷል፤ በዋስትና እና ሌሎች የመብት ጉዳዮች ላይ የተነሱ አቤቱታዎችን ለመስማት በሚል ፍ/ቤቱ ለፊታችን ሰኞ ጠዋት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 7/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አሳዬ ደርቤ ሀምሌ 7/2015 ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ወንጀል ችሎት ቀርቧል። በእለቱም ሰባት ተደራራቢ ክሶች የቀረበበት ሲሆን ጠበቆች ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት በዋስትና እና ሌሎች የመብት ጉዳዮች ላይ የተነሱ አቤቱታዎችን ለመስማት በሚል ለሰኞ ሀምሌ 10/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ እንዲገኙ ሲል ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዐቃቢ ህግ በደራሲ አሳዬ ላይ ያቀረባቸው ሰባት ክሶችም የሚከተሉት ናቸው:_ 1) “ገዳም ዉስጥ ያሉ መነኮሳትን የፊጥኝ አስሮ የሚረሽነዉና በቪዲዮ ቀርጾ አረመኔነቴን ተመልከቱልኝ የሚለዉ የዓብይ ሰራዊት ከአማራ ክልል ተጠራርጎ መዉጣት ይገባዋል” በማለት የጻፈ በመሆኑ በፈጸመዉ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ተከሷል፡፡ 2) “መንግስት ከህ.ወ.ሃ.ት ጋር በፕሪቶሪያ ስምምነት ያደረገዉ በሃገሪቱ ሰላም ለማምጣት አይደለም ዉይይቱ የተደረገዉ እስቲ ደግሞ አንድ ላይ ሆነን አማራን እንዴት እናጥቃ በሚል ነዉ የተደረገዉ፡፡ አማራ ላይ እየተደረገ ያለዉን ነገር መንቃት አለብን……በላይ ዘለቀን ለመሆን _ ሞክር! … ለነፍስህ ለልብህ ንገረዉ….ለራስህ ንገረዉ…..ወገኖቼ መከራ እየበሉ ነዉ …እየመጣብን ያለዉ መከራ ባርነት ከህይወት ቀርቶ ከሞት አይከብድም እንዴ ብለህ ጠይቀዉ ዉስጥህን……የሰላማዊ የትግል ሜዳ አብቅቶለታል” በማለት ንግግር ያደረገ በመሆኑ በኮምፒዉተር አማካኝነት መንግስት ላይ ወንጀል እንዲፈጸም የማነሳሳት መከራ ወንጀል ተከሷል። 3) “በብልጽግና ስርዓት የሙስሊሞችን ያህል ተጠቂ የሆነ የለም በተለይም የአማራ ሙስሊሞች፡፡ ገዢዉ ፓርቲ የአማራ የትግል አመራሮችን ለመግደል _ ከፍተኛ ስምሪት ሰጥቶ የደህንነት ሃይል ተሰማርቶ እየሰራ ነዉ፤ ስምሪት ተሰጥቶ የአማራ ልዩ ሃይል ማልያ ተሰጥቶት የገባ አለ። የአማራ ጀግኖችን የመግደል የመረሸን ስነ-ስርዓት በማከናወን ገዢዉ ፓርቲ ከመጠን በላይ ቋምጦ ምራቁን እያዝረከረከ በአማራ ክልል ላይ ከፍተኛ አሰሳ እያከናወነ ነዉ፡፡ አማራ ክልልን የማጥፋት ዘመቻ ዉስጥ የአማራ ብልጽግና በሚል ስም የሚንቀሳቀሰዉ ሃይል የፕሮጀክት መሪ ሆኖ እየሰራ ያለዉ ብ.አ.ዴ.ን ነዉ። ዕቅድ ወጥቶ ተሰጥቶት አማራ ክልልን በተለያየ ስልት ህዝቡን እጅ እግሩን አስሮ ጀግኖቹን በልቶ ትጥቁን አስፈትቶ ለኦሮሙማ ለማስረከብ ነዉ ይሄ ሁሉ ግብግብ፤ በማለት በቪዲዮ ተንቀሳቃሽ ምስል ሃሰተኛ መረጃን ያሰራጨ በመሆኑ በፈጸመዉ ሃሰተኛ መረጃን ማሰራጨት ወንጀል ተከሷል፡፡ 4) “ከትጥቅ ማስፈታት ወደ ትጥቅ መስጠት የተሸጋገረዉ ስምምነት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ቪዲዮ ላይ “ገዢዉ መንግስት በሸገር ከተማ ምንም አይነት አማርኛ ተናጋሪ ነዋሪ እንዳይኖር ማፈናቀል “ማባረር ይገባናል የሚል አጀንዳ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነዉ፡፡” በማለት በቪዲዮ ተንቀሳቃሽ ምስል ሃሰተኛ መረጃን ያሰራጨ በመሆኑ፣ 5) “የግርማ የሺጥላን ግድያ መሰረት አድርጎ በሚገርም ሁኔታ እንኳን ህዝብ ቀርቶ ከዚህ ግድያ በስተጀርባ የአማራ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች አሉበት እየተባለ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማይፈለጉ አመራሮች ላይ እርምጃ ለመዉሰድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ አማራ ክልል ላይ የታቀደዉ ጥቃት ከተሳካ በአማራ ክልል ላይ ከወለጋ አምጥተዉ አመራሮችን ለመሾም ነዉ፡፡” በማለት ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨቱ። 6) “የኦነግ ሸኔ ባለቤት ተገኘ እንዴ” በሚል ርዕስ በሰራጨዉ ቪዲዮ ላይ “የኦነግ ሸኔ ማለት ከልዩ ሃይል ልብስ ቀይሮ አማሮችን እንዲጨፈጭፍ መንግስት ስምሪት ሲሰጠዉ የነበረ ስብስብ ነዉ። ኦነግ ሸኔ ንጹሃንን እንዲጨፈጭፍ መንግስት ያደራጀዉ ቡድን ነዉ፡፡” በማለት ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨቱ፣ 7) የጥላቻ ንግግርንና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የዋጣ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 5 እና 74 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ የሚሉት ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply