ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባደረገው ዲስኩር “እነ ስብሓት ነጋ ይፈቱ ሲባል እኔም ደንግጫለሁ” ሲል ተደምጧል። በእነ ስብሐት የመፈታት ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር የተቀመጠው ሰውዬ ከደነገጠ…

ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባደረገው ዲስኩር “እነ ስብሓት ነጋ ይፈቱ ሲባል እኔም ደንግጫለሁ” ሲል ተደምጧል። በእነ ስብሐት የመፈታት ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር የተቀመጠው ሰውዬ ከደነገጠ እነ ስብሐትን ይፈቱ የሚለውን ትዕዛዝ የሰጠው ማነው? በትናንትናው እለት የሻዕብያው አምበል ኢሳያስ አፈወርቂ በትግርኛ ያደረገውን ቃለ መጠይቅ እያዳመጥሁ ነበር። ኢሳያስ አሜሪካ በየአገሩ ልዑክ አድርጋ ስለምትሾማቸው ሰዎች ሲናገር “የአሜሪካ ልዑክ ሥራ ለአገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማዘዝ ነው” ነበር ያለው። ዐቢይ አሕመድ በእነ ስብሓት ነጋ የመፈታት ጉዳይ ከደነገጠ ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳለው እነ ስብሓት ነጋን እንዲፈቱ ያዘዘው አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካው ልዑክ ጀፍሪ ፌልትማን ነው ማለት ነው? የታሪክ ተመራማሪው አቻሜለህ ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply