ባሕር ዳር: ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ116ኛ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ላይ ንግግር አድርገዋል። ፊልድ ማርሻሉ ኢትዮጵያ ረጅም ዕድሜ ያላት ቀደምት እና በትውልድ ቅብብሎሽ የዘለቀች ታላቅ ሀገር መኾኗን ገልጸዋል። በእነዚህ ረጅም የታሪክ ዘመናትም በየትውልዱ በነበሩ ልጆቿ ተጋድሎ ነጻነቷ እና ክብሯ ተጠብቆ የተላለፈችልን ሀገር ናት ብለዋል። […]
Source: Link to the Post