ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኢትዮጵያ ባቀረበችው የብድር ጥያቄ ዙሪያ ከመንግሥት ጋር ውይይቶችን እንደቀጠለ መሆኑን አስታውቋል።የድርጅቱ ልዑካን ቡድን በቀጣዮቹ ሳምንታት በድ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/WNzr6JvN-7zLDNmZlMOTcyWLACkqRcpIyIB8X9jjU-Bp_vB_0bstz6agasrFuJJtBQbSry4YpvbQaKofSOabK7MfGbQri2DrX8LBMIEQY0VK6gq93WMBnUrH-3rk_t5lGMugwICmYyAis_KdYB7p0JWLaKbXHeQOQVNRLs5eTUvgH3zuK87niWXOMOM7aV8sweMd6Di6wfyGwlBRgmUMYoIroq9wwRuVuCpdLH31P_gGQfMIvg3beCFmr2Sp13HifgPqcWt2yGaCNJtKBYSRvbA0L8gelAjHw6Zq2UeIUFZYBMvaR1UX0vuNS6vAHfI1WtB3elHT5aST9ADrM9uy9w.jpg

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኢትዮጵያ ባቀረበችው የብድር ጥያቄ ዙሪያ ከመንግሥት ጋር ውይይቶችን እንደቀጠለ መሆኑን አስታውቋል።

የድርጅቱ ልዑካን ቡድን በቀጣዮቹ ሳምንታት በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዝ የድርጅቱ ኃላፊዎች ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

የድርጅቱ ልዑክ ባለፈው ጥቅምት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በብድር ጥያቄው ዙሪያ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገሩ ይታወሳል።

መንግሥት እስከ መጋቢት መገባደጃ ድረስ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ብድር ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር እስከ መጋቢት ወር የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰች ግን፣ አበዳሪ አገራት እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት ድረስ ያራዘሙላትን የብድር እፎይታ ሊሰርዙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply