ዓለም ቀልቡን ወደ ሶማሊያና አፍሪካ ቀንድ እንዲያዞር አቡነ ፍራንሲስ አሳሰቡ

https://gdb.voanews.com/019e0000-0aff-0242-de62-08da7eee69aa_tv_w800_h450.jpg

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ትናንት፤ ዕሁድ በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባሰሙት መልዕክት በሶማሊያና በአካባቢዋ በሚገኙ አገሮች እየደረሰ ያለው ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ “የዓለም አቀፉን ማኅብረሰብ ትኩረት እንዲስብ” ጥሪ አሰምተዋል።

በሌላ በኩል አፍሪካ ቀንድ ላይ በበረታው ድርቅ ምክንያት ሚሊዮኖች ለተፈናቀሉባት ሶማልያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት የላከው አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከትናንት በስተያ ሞቅዲሾ ገብቷል።

ከሞቅዲሾና ከቫቲካን የተጠናቀሩ ዘገባዎችን ደረጀ ደስታ አቀናጅቷቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply