You are currently viewing ዓለም አቀፍ ለጋሾች ችግር ውስጥ ያለውን የአፋር ህዝብ አልፈው “ትግራይን እንርዳ” ማለታቸው አግባብ አይደለም ሲል የአፋር ክልል ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 23 ቀን 201…

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ችግር ውስጥ ያለውን የአፋር ህዝብ አልፈው “ትግራይን እንርዳ” ማለታቸው አግባብ አይደለም ሲል የአፋር ክልል ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 23 ቀን 201…

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ችግር ውስጥ ያለውን የአፋር ህዝብ አልፈው “ትግራይን እንርዳ” ማለታቸው አግባብ አይደለም ሲል የአፋር ክልል ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር በመሆናቸው የተዘረፈውን ሀብት ማወቅ አልተቻለም ተብሏል። “የአፋር ሕዝብ እንደ ፍየል እና እንደዝንጀሮ በየቦታው ፈሶ እሱን ወደኋላ አድርገን የትግራይ ሕዝብ ብቻ ይረዳ የሚል ቋንቋ ትክክል” አይደለም ሲል የአፋር ክልል በዓለምአቀፍ ለጋሾች ላይ ቅረታውን አቅርቧል፡፡ የአፋር ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብ እንደገለጹት በአፋር ክልል በርካታ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በየቦታው ነው ያሉት፡፡ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በየቦታው እየወለዱ፤ ለውኃ ጥምና ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውንም ተናግረዋል፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ ለጋሽ አካላት በአፋር አልፈው ዕርዳታ ለትግራይ ሕዝብ ማድረስ እንደሚፈልጉም የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ዕርዳታ ማግኘት እንዳለበትና መጎዳት እንደሌለበት እንደሚያምኑ የገለጹት ኃላፊው፤ አፋር ክልል ላይ በችግር ውስጥ የፈሰሰውን ህዝብ ጥሎ ማለፍ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አቶ ያሲን ሀቢብ የአፋር ሕዝብ እንደሌላው ጉልበትና የዓለም ሚዲያ እንደሌለው አንስተው “እኛ ግን የምንችለውን ሁሉ እንሰራለን” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከጤና እና ከሰብዓዊነት አንጻር አፋር ክልል ላይ የፈሰሰውን ህዝብ ጥሎ ማለፍ አስቸጋሪ እንደሆነም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ “እኛ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ችግር የለብንም፤ ቢረዳም ችግር የለብንም፤ እኛ የምናየው ከጤናው ረገድ ነው” የሚሉት ኃላፊው የአፋር ሕዝብ ድጋፍ ሳያገኝ እሱን በማለፍ ትግራይን ብቻ እንርዳ የሚለው ጉዳይ “ትንሽ ከእርዳታ አለፍ ያለ ሌላ ነገር ነው የሚመስለው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እንደክልል መንግስት እየተሰራበት መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት በአፋር ክልል አንድ ሆስፒታል፣ 21 ጤና ጣቢያዎች፤ 55 ጤና ኬላዎች በህወሃት ኃይሎች መዘረፋቸውንም የጤና ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በጦርነት ከወደሙት የጤና ተቋማት መካከል 17 ጤና ጣቢያዎች እና 30 ጤና ኬላዎች እንዲሁም አንድ ሆስፒታል ስራ እንዲጀምሩ መደረጉን የክልል ጤና ቢሮ አስታውቋ፡፡ አሁን ላይ ወደ አገልግሎት የተመለሰው የከልዋን ሆስፒታል ሲሆን ጭፍራ ጤና ጣቢያን ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑም ክልሉ ገልጿል፡፡ እንደክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ገለጻ በአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች በህወሃት ቁጥጥር ስር ስለሆኑ ምን ያህሉ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም፡፡ አል ዐይን አማርኛ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply