ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን “ሙዚየሞች ለትምህርት እና ለምርምር” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ47 ግዜ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ግዜ…

ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን “ሙዚየሞች ለትምህርት እና ለምርምር” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ47 ግዜ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ግዜ በዛሬው እለት ግንቦት 9 /2016 በኢትዮጵያ ቅርስ ባለ ስልጣን አዘጋጅነት በመከበር ላይ ይገኛል።

እለቱ ሲከበር ሙዚየሞች ትኩረት እንዲያገኙ እና ያልታዩት እንዲታዩ የማድረግ አንዱ አላማው መሆኑ ተነስቷል።

የሙዚየም ዋነኛው ስራ ማስተማር ሲሆን ለሀገር ግንባታ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተገልጿል።

ሙዚየሞች አንድነታችንን የሚያጠናክሩልን በመሆናቸው ልንንከባከባቸው እና ልንጎበኛቸው እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ወደፊት ሙዚየሞች የሚጎበኙበት ሰአት የማሻሻል እና ከስራ ሰአት ውጪ ሰዎች መጎብኘት የሚችሉበት ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሆነም ሰምተናል።

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply