ዓለም አቀፍ የከፍተኛ የደም ግፊት ቀን ለ16ተኛ ጊዜ  በሀገራችን በትናንትናው እለት ተከብሯል።ትናንት የተከበረው አለም አቀፍ ከፍተኛ የደም ግፊት ቀን ደም  ግፊትዎን ይለኩ፣ ደም ግፊትዎ…

ዓለም አቀፍ የከፍተኛ የደም ግፊት ቀን ለ16ተኛ ጊዜ  በሀገራችን በትናንትናው እለት ተከብሯል።

ትናንት የተከበረው አለም አቀፍ ከፍተኛ የደም ግፊት ቀን ደም  ግፊትዎን ይለኩ፣ ደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ  እና እረጅም እድሜ ይኑሩ  በሚል መሪ ቃል ነው።

በዓለማችን ለ20 ኛ ጊዜ  በኢትዮጲያ ለ16ኛ ጊዜ  የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የከፍተኛ የደም ግፊት ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል፡፡

በመግለጫው ላይ  በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር  መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሂወት ሰለሞን  የተገኙ ሲሆን፤ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እና የሚያደርሱት ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን ተናረዋል፡፡

በዓሉን አስመልክቱ ከኩላሊት ህመም ማህበር እና ከኢትዮጲያ የልብ ህሙሟን ማህበር  ጋር በጋራ በመሆን የደም ግፊትን የመለካት  ስራዎች እንደሚከናወኑ ተነግሯል፡፡

በመሆኑም በዓሉን በየዓመቱ በማክበር ብቻ ለውጥ የማይመጣ መሆኑ በመድረኩ ላይ የተነገረ ሲሆን፤ ዜጎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን እንደ ደም ግፊት፣ የስኳር እና የልብ ህመምን የመመርመር ልማድን ማዳበር እንደሚገባቸው ተመላክሏል፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች ለልብ ህመም ፣ ለደም ስር ጥበት እና ለኩላሊት ህመም  አጋላጭ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች የሚውሉ የመመርመሪያ መሳሪያዎችነን  በበቂ ሁኔታ እንዲዳረሱ ጥረቶች የማድረግ እና የባለሞያዎች አቅም የመፍጠር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply