ዓለም እና ፅንፈኝነት (አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም)  ሂትለርም ሆነ ሞሶሎኒ ሀገራቸውን አብዝተው ይወዳሉ፡፡ ሀገራቸውን የሚወዱት ግን ሌላውን በመጥላት ነው፡፡ ሂትለር ጀርመን በምድር…

ዓለም እና ፅንፈኝነት (አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም) ሂትለርም ሆነ ሞሶሎኒ ሀገራቸውን አብዝተው ይወዳሉ፡፡ ሀገራቸውን የሚወዱት ግን ሌላውን በመጥላት ነው፡፡ ሂትለር ጀርመን በምድር…

ዓለም እና ፅንፈኝነት (አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም) ሂትለርም ሆነ ሞሶሎኒ ሀገራቸውን አብዝተው ይወዳሉ፡፡ ሀገራቸውን የሚወዱት ግን ሌላውን በመጥላት ነው፡፡ ሂትለር ጀርመን በምድር የተለየ ፍጡር ነው ካለ በኃሏ፣ አይሁዳዊያን ግን የምድራችን ተውሳኮች ናቸው ሲል ተፈላሰፈ፡፡ ጀርመን ትቅደም ብሎ ከእንግሊዝ እስከ ሩሲያ ለመጠቅለል የጦርነት ነጋሪት ጎሰመ፡፡ ፅንፈኝነት በባህሪው ነጣይ እና ምክንያታዊ ስላልሆነ የውድመት ውጤትን ይዞ ይመጣል፡፡ ሂትለር ዓለምን ለመጠቅለል ታግሎ የጀርመንን ዋና ከተማ በርሊንን እንኳን ማዳን አልቻለም ነበር፡፡ ምዕራባዊ በርሊን አሜሪካ ስትወስድ፣ ምስራቃዊ በርሊን ሩሲያ ወሰደች፡፡ በአሜሪካው እና በሩሲያው በርሊን መካከል ታላቁ የበርሊን አጥር ታጥሮ የሂትለር ሜዳ የቀዝቃዛው ጦርነት ማዕከል ሆነ፡፡ የሂትለር ፅንፈኝነት ጀርመንን ለ40 ዓመት ወደ ኃላ ጎትቷታል፡፡ የእነ ጆሴፍ ስታሊን ፅንፈኝነትም ታላቋ ሶብየት ህብረትን ከ15 እንድትቆራረጥ አድርጓታል፡፡ የህወኃት እብሪታዊ ፅንፈኝነትም አይወድቁ አወዳድቅ የወደቀው ከምክንያት እና ከሰውነት የተጣላ መሆኑ ነው፡፡ በድሎት የኖሩት የህወኃት አመራሮች ተመልሰው በሰቀቀን፣ በውሃ ጥም እና ርሃብ ወደ ጫካ ወርደዋል፡፡ ቄስ እና ሼህ መስለው የነገን ፅሃይ ለመሞቅ በስጋት ውስጥ ናቸው፡፡ ህወኃት ዘርፎ እና ያበጀው ስራዓት ከምኒሊክ ቤተመንግስት ሳይጠፋበት ፅንፈኝነቱ ግን እውነቱን ጋርዶበት በራሱ መከላከያ ላይ ጦር አወጀበት፡፡ በመጨረሻም በሽምግልና ዘመናቸው የህወኃት አመራሮች ተቅበዝባዥ እና ደንጋጣ ሆነው በመሯት ሀገር መሳደድ እጣ ክፍላቸው ሆነ፡፡ ያሳደዱት ሁሉ መሪያቸው ሆነ፡፡ ግዛታቸውን ቀርቶ የግል መጠለያቸውን ማስተዳደር አልችል ብለው ጫካ መኖሪያቸው ሆነ፡፡ የታላቋ የአሜሪካ ፕሬዜዳንትም ዶናልድ ትራንፕ በፅንፈኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡ አሜሪካ ትቅደም መርሆቸው ነው፡፡ አሜሪካን እንደገና ማተለቅ በሚለው ህልማቸው ውስጥ አሜሪካ ደህና ከሆነች ሌላው ዓለም አይመለከተኝም አሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታትን፣ የዓለም የጤና ድርጅትን፣ የአትላቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የሆነውን – ኔቶን፣ የአፍሪካ ህብረት ብቻ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ድርጅት እያጥላሉ አሜሪካ ብቻ አሉ፡፡ አሜሪካን በፅንፈኝነታቸው ከሌላው ዓለም ነጥለው ሰማያዊ እና ቀያይ በሚል በዴሞክራቶቸ እና በሪፒሊካችን መካከል የልዮነት አጥር አበጁ፡፡ ዛሬ ሌሊት አሜሪካ ወደ እርስ በእርስ ገባችና እና በዋሽንግተን ዲሲ የአስቸኳይ አዋጅ ታወጀ፡፡ ትራንፕ መጀመሪያ አሜሪካን ከዓለም ለመነጠል ሞከሩ፡፡ ከዚያ በኃላ ደግሞ አሜሪካውያንን እርስ በእርሳቸው ነጣጠሉ፡፡ ፅንፈኝነት በባህሪው አግላይ፣ነጣይ፣ ኢ- ምክንያታዊ በመሆኑ በመጨረሻው የውድቀት መንገድ ሆኖ ይቋጫል፡፡ በኢትዮጵያ ኦነግ ለ60 ዓመት ታግሎ የ 42 ዓመቱ አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ኦነግ አካታች መንገድ ስለሌለው እና እንደ ኢትዮጵያ ለመኖር ስለሚሰፋበት ነው፡፡ ህልሙ ስላልተሳካለት ሁሌ ማኩረፍ፣ሁሌ ንፁሃንን መግደል ባህሪው ሆነ፡፡ በዛሬው ዕለት እንኳን ከ130 ዓመት በፊት ጡታችን ተቆርጧል ብለው የጨለንቆን ቀን እየዘከሩ ነው፡፡ አኖሌን እየባረኩ ነው፡፡ ጨለቆን እያወገዙ ራሳቸው በዚህ ዘመን ከተረቱ የአኖሌ ታሪክ የባሰ በተግባር ጡት ይቆርጣሉ፡፡ ሰው ያርዳሉ፡፡ ይህ ፅንፈኝነት የሚወልደው የብሶት ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡ አምራቹ ወለጋ ዛሬ ማሳው ተቃጥሏል፡፡ ገበያው እንደ ወትሮው አልሞቀም፡፡ ፅንፈኝነት የሰውልጆች የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የሀገራት መፈራረስ እና የመንግስታት መበስበስ መንስዔ ነው፡፡ ዛሬ በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የሚደረሰው ጅምላ ግድያ መንስዔው ፅንፈኝነት መሆኑ ያደረ እውነት ነው፡፡ ፅንፈኞች በሀገር ላይ የከፋ ውድመት እንዳያደርሱ ቀድሞ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋም አቋቁሞ መታገል እና ማረም ከታሪክም ከዛሬም የምንረዳው ሀቅ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply