ዓውድ ዓመትን ዓውድ ዓመት ከሚያስመስሉ ነገሮች መካከል የሚዘጋጁ ምግብ እና መጠጦች ከፍ ያለ ድርሻ አላቸው።
የወዳጅ ዘመድ መጠያየቅ፣ የቡናው መጫጫስ፣ የቄጠማው መጎዝጎዝ እና የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በምግብ እና በመጠጡ ላይ የሚጨመሩ ሰበዞች ናቸው።
በተለይ እንደ ገና እና ፋሲካ ያሉ ትላልቆቹ ዓውደ ዓመቶች የሚመጡት ረዥም የጾም ወቅትን ተከትለው በመሆናቸው አቅም በፈቀደ ሁሉ እርድ ይከናወናል።
ከዚያ በኋላ ዳቢት ከሻኛ መቁረጥ፣ ጥብስ ከክትፎ እያመራረጡ ማወራረድ፣ ቀዩን ካልጫው እያጣቀሱ መጉረስ የዓውድ ዓመት ቱርፋቶች ናቸው።

Source: Link to the Post