
ዘመነ ካሴ አማራነት የተከበረበት እንጅ አማራነት የሚሰዋለት ኢትዮጵያዊነት የማያዛልቅ ጉዞ እንደሆነ ከጠዋቱ የገባው የንቁው አማራ ትውልድ ምልክት ነው። ለኢትዮጵያዊነትም ቢሆን የስልጣን ተስፋውን አሽቀንጥሮ፣በህዝቡ ለቅሶ ላይ የሚታጨደውን የደስታ አዝመራ እርም ነው ብሎ፣ ጠመንጃውን አንግቶ ጫካ የገባ ጎበዝ ነው። ዘመነ የሁሉን ወሰን ያውቃል።ሚዛናዊ ነው።ነበልባል አንደበቱ ጨዋነትንም አሰናስሏል። ሲናገር በጆሮ ሳይሆን በልብ እንዲደመጥ አድርጎ ነው።ልብ ያለው ብቻ ዘመነ የሚለው ይገባዋል! ሆኖም ቀድሞ መንቃቱ እዳ ሆኖበት ይሳደዳል። የዘመነ ወንጀል ለአማራ ህዝብ መቆሙ ነው! የቆመለት ህዝብ ጀግናውን ያስፈታ ዘንድ ግድ ነው! #ዘመነ_አማራ… #freezemenekassie
Source: Link to the Post