ዘመነ ካሴ የ7 ቀናት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰጠው

ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዘመነ ካሴ ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2015 በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በድጋሜ ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን፤ በተሰጠኝ 10 ቀናት ውስጥ ምርመራዬን ማጠናቀቅ አልቻልኩም በማለት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።

የዘመነ ካሴ ጠበቆችም ወንጀል የተባለዉን ጉዳይ ለማጣራት በሚል ፖሊስ ላለፉት አራት ወራት ያጣራ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት ውሎ የፈቀደው 10 ቀናት በቂ መሆኑን እንዲሁም ሌሎችን መከራከሪያዎች በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት አያስፈልግም በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ዘመነ ካሴ በዋስ እንዲለቀቅ ለፍርድ ቤቱ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም ያለው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ፤ መርማሪ ቡድኑ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ የ7 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ፖሊስ እስከ ጥቅምት 01 ቀን 2015 ድረስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ ትዕዛዝ መስጠቱን አዲስ ዘይቤ ዘግባለች። ዘመነ ካሴም ወደ ባህር ዳር ማረሚያ ቤት መመለሱ ታውቋል።

መስከረም 11 ቀን 2015 በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘመነ ካሴ መስከረም 12 ቀን ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፤ ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ዘመነ ካሴ “ህገ ወጥ ቡድን በማደራጀት እና “ኬላ ዘርግቶ ገንዘብ በመሰብሰብ” እንዲሁም “በፌስ ቡክ ቅስቀሳ ማድረግ” በሚሉ ወንጀሎች መጠርጠሩን መግለጹ ይታወሳል።

The post ዘመነ ካሴ የ7 ቀናት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰጠው first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply