ዘመናዊው የቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ ነዉ ተባለ፡፡የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞቹ የሚተክላቸውን የኢነርጂ ቆጣሪ ሜትሮችን የመለካት ብቃትና ጥራት ለማረጋገጥ የሚ…

ዘመናዊው የቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ ነዉ ተባለ፡፡

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞቹ የሚተክላቸውን የኢነርጂ ቆጣሪ ሜትሮችን የመለካት ብቃትና ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊ የቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያ ተግባረዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ተግባረዊ የሚደረገው አውቶማቲክ ቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያ ባለ ሶስት ፌዝ እና ፖላንድ ሰራሽ የ2021 ሞዴል ሲሆን የቆጣሪ ጥራትን ለማረጋገጥና ሜትሮች አስተማማኝ የመለካት ብቃት ኖሯቸው ረዥም እድሜ እንዲኖራቸው የሚደርግ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያው አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 120 ቆጣሪዎችን ፈትሾ ብቃታቸውን ማረጋገጥ የሚችል ነው።

አውቶማቲክ ቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያው ሁሉንም አይነት የኢነርጂ ቆጣሪዎችን ማለትም የድህረና ቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን፣ ስማርት፣ ኤሌክትሮሜካኒካል ወይም ኤሌክትሮኒክ ቆጣሪዎችን መመርመር የሚችል ሲሆን እስከ 480 ቮልት እና እስከ 240 A ከረንት መፈተሽ ይችላል።

መፈተሻ መሳሪያው ብዙ የታሪፍ መደቦችን በአንድ ጊዜ ማረጋገጥ የሚችል ሲሆን እስከ 16 ታሪፎችን ማረጋገጥ ይችላል፡፡

ተግባራዊ የሚደረገው የቆጣሪ መፈተሻ መሳሪያ ሶስት ቤንች ያለው ሲሆን እያንዳንዱ ቤንች በአንዴ 40 ቆጣሪ ይፈትሻል። እንደፍተሻው አይነት በአንድ ባች ከ30 እስከ 60 ደቂቃ የሚወስድ ነው።

ከዚህ በፈት ተቋሙ ሲጠቀምበት የነበረው የቆጣሪ ጥራት ፍተሻ መሳሪያ በአንድ ጊዜም የ20 ቆጣሪዎችን ጥራት ብቻ የሚፈትሽ ከመሆኑም በላይ የፍተሻ ሂደቱ አዝጋሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply